Tuesday, December 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተቀሰቀሰው ግጭት ስምንት ሰዎች እንደ ሞቱ ክልሉ አስታወቀ

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተቀሰቀሰው ግጭት ስምንት ሰዎች እንደ ሞቱ ክልሉ አስታወቀ

ቀን:

  • ሌሎች ምንጮች ቁጥሩን ከፍ አድርገዋል

ሐሙስ ጥቅምት 16 ቀን 2010 ዓ.ም. በቤንሻንጉል ጉሙዝ ከማሺ ዞን ሃሮ ዴዴሳ ቀበሌ በተነሳው ግጭት ስምንት ሰዎች መሞታቸውን ክልሉ አስታወቀ፡፡

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ መንግሥቱ ቴሶ የሟቾች ቁጥር ስምንት ብቻ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ስምንት ሰዎች ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸው በሕክምና ላይ እንደሚገኙ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ዜጎች ደግሞ ግጭቱን በመፍራት በየቤተ እምነቶች ተጠልለው እንደሚገኙ አቶ መንግሥቱ አክለዋል፡፡

እንደ አቶ መንግሥቱ ገለጻ ግጭቱ የተቀሰቀሰው በአማራና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ተወላጆች መካከል ነው፡፡ ‹‹አንድ ግለሰብ በሌላ ሰው አማካይነት ሕይወቱ ስለጠፋ ቀብሩ ከተፈጸመ በኋላ፣ ቤተሰቦቹና ዘመዶቹ በደም ፍላት ተነሳስተው በግለሰቡ ቤተሰቦች ላይ ጉዳት ለማድረስ ተንቀሳቅሰዋል፤›› ብለዋል፡፡

በዚህም የተነሳ ስምንት ሰዎች ሕይወታቸው እንዳለፈ ተናግረዋል፡፡ በግጭቱ በዋናነት ተጎጂ የነበሩት የአማራ ብሔር ተወላጆች እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሌሎች ምንጮች ግን የሟቾች ቁጥር አሥር እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡ አንድ ታማኝ የሪፖርተር ምንጭ 80 ቤቶች ሙሉ በሙሉ መቃጠላቸውንና ከፍተኛ የድብደባ ጉዳት የደረሰባቸው አሥራ ሁለት ግለሰቦች በነቀምት ሆስፒታል በሕክምና ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡ በግጭቱ ከ200 በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውንም ጠቁመዋል፡፡

አቶ መንግሥቱ ግጭቱ ብሔር ተኮር አይደለም ቢሉም፣ ግጭቱ ተቀስቅሶ የነበረው በአማራና በጉሙዝ ብሔረሰብ መካከል እንደነበር መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

በ2006 ዓ.ም. በሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ብሔር ተወላጆች ከጉሙዝ ብሔረሰብ ጋር ተፈጥሮ በነበረ ብሔር ተኮር ግጭት፣ ወደ ክልላቸው ተመልሰው እንደነበር ይታወሳል፡፡

በግጭቱ ጉዳት የደረሰባቸውን የአማራ ብሔር ተወላጆች ሁኔታ ለማየትና እገዛ ለማድረግ የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ቡድን ወደ ሥፍራው አቅንቶ እንደነበር የሪፖርተር ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ አምስት ሰዎችን እንደያዘ የተገለጸው የክልሉ ልዑካን ቡድን ጉዳት የደረሰባቸውና የተፈናቀሉ ዜጎችን ከመጎብኘት በተጨማሪ፣ ከተጎጂዎች ጋር ውይይት ማድረጉ ታውቋል፡፡

በውይይቱ ወቅትም የአማራ ክልል መንግሥት ጉዳት የደረሰባቸውንና ንብረታቸው የተቃጠለባቸውን ዜጎች እንዲያቋቁም ጥያቄ እንደቀረበለት ተገልጿል፡፡

በግጭቱ የተጎዱ ዜጎች በአብዛኛው ከምዕራብ ጎጃም አካባቢ የሄዱና በሥፍራው ለረዥም ዓመታት የኖሩ በመሆናቸው ከጉሙዝ ብሔረሰብ ጋር በፍቅር ይኖሩ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡

አቶ መንግሥቱ በአሁኑ ወቅት መረጋጋት መፈጠሩን ቢናገሩም፣ ሌሎች ሥፍራዎች የተጠለሉ ግን ወደ ቀዬአቸው እንዳልተመለሱ ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...