Monday, October 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአቶ በቀለ ገርባ ዋስትና መታገድ እያነጋገረ ነው

የአቶ በቀለ ገርባ ዋስትና መታገድ እያነጋገረ ነው

ቀን:

ከአንድ ዓመት በፊት በሽብር ተግባር ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው፣ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ፣ የተከሰሱበት የሽብርተኝነት አዋጅ አንቀጽ ተቀይሮ ዋስትና ቢፈቀድላቸውም ሳይለቀቁ በይግባኝ መታገዱ እያነጋገረ ነው፡፡

አቶ በቀለ ተጠቅሶባቸው የነበረው የሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 3(1፣ 3፣ 4፣ 6) ወደ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 257(ሀ)፣ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ሲቀየር፣ አንቀጹ ዋስትና ስለማያስከለክል ሕገ መንግሥታዊ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠይቀዋል፡፡

ብዙ የውጭ ግንኙነት ስላላቸው ከአገር ከወጡ ተመልሰው ክርክራቸውን በአግባቡ ያደርጋሉ የሚል እምነት እንደሌለው ዓቃቤ ሕግ ገልጾ፣ ዋስትናቸው ውድቅ እንዲደረግና በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከላከሉ ያቀረበው መከራከሪያ ሐሳብ ተቀባይነት በማግኘቱ፣ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ መደረጉ ይታወሳል፡፡

የዓቃቤ ሕግ ተቃውሞ ተቀባይነት አግኝቶ የዋስትና መብታቸው የታለፈባቸው አቶ በቀለ፣ በውሳኔው ቅር በመሰኘታቸው ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በጠበቃቸው አቶ አመሐ መኰንን አማካይነት ይግባኝ ብለው ነበር፡፡

ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዳዩ ያስቀርባል ካለ በኋላ፣ ሁለቱንም ወገኖች አከራክሮ ባለፈው ሳምንት ጥቅምት 20 ቀን 2010 ዓ.ም. በ30 ሺሕ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ውሳኔ ሰጥቶ ነበር፡፡

ይግባኝ ሰሚው ችሎት የሰጠው ውሳኔ ቤተሰቦቻቸውን፣ ጓደኞቻቸውንና ደጋፊዎቻቸውን ከማስደሰትና በተለያዩ ድረ ገጾችና በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ቀዳሚ ዜና ከመሆናቸው በስተቀር፣ ተከሳሹ ከእስር ሊፈቱ አልቻሉም፡፡ በአንድ ቀን ልዩነት የአቶ በቀለ ገርባ የዋስትና ፈቃድ እንደታገደ በመሰማቱም ‹‹ለምን?›› እና ‹‹እንዴት?›› የሚሉ ጥያቄዎችን ፈጥሮ መነጋገሪያ ሆኖ ቀጥሏል፡፡

ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ የሥር ፍርድ ቤቶች ማለትም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ መቀየር የማይገባውን የፀረ ሽብርተኛነት አዋጅ አንጾችን ወደ መደበኛ ሕግ ቁጥር መቀየሩ፣ ይግባኝ ሰሚው ችሎት ደግሞ የተከለከለን የዋስትና መብት መፍቀዱ፣ መሠረታዊ የሕግ ስህተት መሆኑን በመግለጽ ያቀረበው ማመልከቻ ተቀባይነት አግኝቶ፣ ሰበር ችሎቱ ዋስትናው እንዲታገድ ትዕዛዝ በማስተላለፍ ለኅዳር 14 ቀን 2010 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡  

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...