አስፈላጊ ግብዓቶች
- 1 ኩባያ መረቅ፣ የዶሮ ወይም የሥጋ
- 1/4 ኩባያ ኮምጣጤ
- 1/4 ኩባያ ስኳር
- 1/2 የሻይ ማንኪያ ሽንኩርት የተከፈተ
- 1/2 ኪሎ ዓሳ የተጠበሰ
ጨው በርበሬ፡፡
አሠራር
- መረቅ፣ ኮምጣጤ፣ ስኳር፣ ጨው፣ በርበሬና ሽንኩርት ብረት ድስት ውስጥ ጨምሮ ማደባለቅ፡፡
- የተደባለቀውን እሳት ላይ ጥዶ ያለማቋረጥ እያማሰሉ እስኪወፍር ድረስ ማብሰል፡፡
- የበሰለውን ሶስ የተጠበሰው ዓሳ ላይ ጨምሮ ማቅረብ፡፡
- ጽጌ ዕቁባሚካኤል ‹‹የእናት ጓዳ›› (1984)