Wednesday, October 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -

በለስ

ቀን:

በለስ የተክል ዕንጨት ስም እንደሆነ መዝገበ ቃላቱ ይነግረናል፡፡ በለስ ከወይን ጋራ የሚተከል የሾላ ወገን ወተታም፡፡ ዕንጨቱም ፍሬውም በለስ ይባላል፡፡

በሌላ የድረ ገጽ መድበልም በለስ ቅጠሉ ሰፋፊ፣ ነጭ ፈሳሽ ያለው፣ ፍሬው የሚበላ የዕፀዋት አስተኔ ይለዋል። ፍሬውም ደግሞ በለስ ወይም ዕፀ በለስ ይባላል።

በበለስ ቤተሰብ ውስጥ ካሉት የተለያዩ  የዛፍ ዓይነቶች  መካከል ተራ በለስየቆላ በለስየቊልቋል በለስ ይጠቀሳሉ፡፡  ተራ በለስ ከጥንት ጀምሮ ስለ ፍሬው በእርሻ ወይም በጓሮ ተተክሏል። ፍሬውም ለጤንነት እጅግ መልካም ነው። የቊልቋል በለስ እውነተኛ በለስ ሳይሆን እንዲያውም ቊልቋል ነው። ሆኖም ፍሬውን ስለሚመስል ብዙ ጊዜ ይህም ተክል በለስ ይባላል። በሌላ በኩልም ፍሬው ፍሬው የማይበላ የዱር በለስ ‹‹የውሻ በለስ›› ተብሎ ይጠራል፡፡

በለስ በተለያዩ ሃይማኖቶች  እንደተቀደሰ ዛፍ ይቆጠራል።  ዘፍጥረት አዳም ሔዋን  ልብስ የተሠራላቸው ከበለስ ቅጠል ሲሆን ከገነት የተባበሩትም ዕፀ በለስ በልተው ነበር።

አለቃ ደስታ በማለፊያው አዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት ሥራቸው እንደገለጹት፣ በለስ (በለሶን) ዕፀ አእምሮ (የዕውቀት ዕፅ)፣ የገነት ዛፍ፤ አዳምና ሔዋን ፍሬውን በልተው ቅጠሉን የለበሱት፤ ክፉና መልካም የሚያስታውቅ ነው፡፡

በክርስቲያናዊ ሰምና ወርቅ/ ብሂል የሚጠቀስ ቃል ግጥም እንዲህ ይላል፡፡

‹‹ዕፀ በለስ በልቶ ሔዋን ከንፈርሽ

መድኃኔ ዓለም ልቤ ተሰቀለልሽ››

  • ሔኖክ መደብር
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመገረም እየተመለከቱ አገኟቸው]

ምንድነው እንዲህ ቀልብሽን የሳበው? ስለሰላም ኖቤል ሽልማት ዜና እየተመለከትኩ ነበር። እና...

የወሎ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መመሥረትና የአማራ ክልል ጥያቄ

አማራ የኢሕአዴግ አንዱ መሥራችና አጋር ከሆነው ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ...

የሽንኩርት ዋጋ ሰማይ የነካበት ምክንያት ምንድነው?

ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት የሸማቾችን ኪስ ካስደነገጡ መሠረታዊ ከሚባሉ...

የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ኤግዚቢሽን ማዕከልን እንዲያስተዳድር የተሰጠው ኮንትራት ለምን ተቋረጠ?

በአዲስ አበባ ከተማ ለንግድ ትርዒት ዝግጅት ብቸኛ በመሆን የሚጠቀሰው...