Wednesday, October 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህል12ኛው የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል

12ኛው የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል

ቀን:

12ኛው የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ፊልም ፌስቲቫል (ኢትዮፌስት) በቫድማስ ሲኒማ፣ በአሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴንዝ፣ በፑሽኪንና በሌሎችም የአዲስ አበባ ቲያትርና ሲኒማ ቤቶች ከታኅሣሥ 16 ቀን እስከ 22 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ እንደሚከናወን አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮፌስት ዘንድሮ ‹‹ሳንኮፋ፡ የታሪክ አተራረክ ጥበብ›› በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል፡፡ በኪነ ጥበብ ሥራዎች ላይ ኢትዮጵያዊ አሻራ ለማኖር የሚያስችል የአጻጻፍና የአተራረክ ዘዬ ይኖር ዘንድ ለማመላከትን እንዳለመ አዘጋጆቹ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡  ‹‹ሳንኮፋ›› በአፍሪካ የምትገኝና ወደ ኋላ እያየች ወደፊት የምትበር ወፍ ስትሆን፣ በፈልሙ  ወደፊት የሚደረገውን ግስጋሴ የተሳካ ለማድረግ ሥረ መሠረቱ አስፈላጊ መንደርደሪያ እንደሆነ የፌስቲቫሉ ዳይሬክተር ይርጋሸዋ ተሾመ ተናግሯል፡፡

ሳምንቱን ለሕዝብ ክፍት በሚሆኑበት አዳራሾች ወደ 70 የሚጠጉ ከተለያዩ አገሮች የተውጣጡ ተራኪ፣ አጭር፣ ዘጋቢ፣ አኒሜሽን፣ ዘመን ተሻጋሪና ዘመናዊ ፊልሞች ይቀርባሉ፡፡ የፊልም ጥበብንና ዕድገቱን የተመለከቱ ዐውደ ጥናቶች፣ ሴሚናሮችና ውይይቶች በዘንድሮው መርሐ ግብር ውስጥ ተካተዋል፡፡ ፌስቲቫሉ የሚጠናቀቀው በኢትዮጵያ ፊልም ባለሙያዎች መካከል በሚደረግ ውድድር ላሸነፉት በሚበረከት የሽልማት ሥነ ሥርዓት ነው፡፡

ለአሸናፊ የፊልም ባለሙያዎች በሽልማት የሚበረከቱትን ዋንጫዎች የኢትዮጵያ ተምሳሌት የሆኑ ስያሜዎቻቸውን እንደሚይዙም ተገልጿል፡፡ እነዚህም፣  ለምርጥ ተራኪ ፊልም ‹‹ጥቁር አንበሳ››፣ ለምርጥ ዳይሬክተር ‹‹ሳባ/ኢትዮጵያዊ ዓይን››፣ ለምርጥ የፊልም ጽሑፍ  ‹‹ግዕዞፒያ››፣ ለምርጥ ሲኒማ ቀረፃ ጥበብ ‹‹ቀስተ ደመና››፣ ለምርጥ ተዋናይት ‹‹ድንቅነሸ››፣ ለምርጥ ተዋናይ ‹‹ድንቅነህ›› ናቸው፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመገረም እየተመለከቱ አገኟቸው]

ምንድነው እንዲህ ቀልብሽን የሳበው? ስለሰላም ኖቤል ሽልማት ዜና እየተመለከትኩ ነበር። እና...

የወሎ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መመሥረትና የአማራ ክልል ጥያቄ

አማራ የኢሕአዴግ አንዱ መሥራችና አጋር ከሆነው ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ...

የሽንኩርት ዋጋ ሰማይ የነካበት ምክንያት ምንድነው?

ባለፉት ሁለትና ሦስት ሳምንታት የሸማቾችን ኪስ ካስደነገጡ መሠረታዊ ከሚባሉ...

የአዲስ አበባ ንግድ ምክር ቤት ኤግዚቢሽን ማዕከልን እንዲያስተዳድር የተሰጠው ኮንትራት ለምን ተቋረጠ?

በአዲስ አበባ ከተማ ለንግድ ትርዒት ዝግጅት ብቸኛ በመሆን የሚጠቀሰው...