Friday, June 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊከአኗኗር ምርጫ ጋር በተያያዘ በየዓመቱ 16 ሚሊዮን ሰው ይሞታል

ከአኗኗር ምርጫ ጋር በተያያዘ በየዓመቱ 16 ሚሊዮን ሰው ይሞታል

ቀን:

ሲጋራ ማጨስ፣ አብዝቶ አልኮል መጠጣት፣ ከመጠን በላይ የስብና የስኳር ይዘት ያላቸውን ምግቦች አዘውትሮ መጠቀም፣ ለሰው ልጆች የሕይወት ህልፈት የመጀመሪያና ዋነኛ ምክንያት እንደሆኑ የዓለም አቀፉ የጤና ተቋም (WHO) አስታወቀ፡፡ ከአኗኗር ሁኔታ ጋር ተያይዞ የሚከሰቱ በሽታዎች ከማንኛውም ወረርሽኝ በበለጠ ለሰው ልጅ የጤና መቃወስ ብሎም ህልፈት መንስዔ መሆናቸውን የገለጹት የዓለም አቀፍ ጤና ተቋም የበሽታ መከላከልና ቁጥጥር ኃላፊ ሻንዚ ሜንዲስ ናቸው፡፡ ከሰው ወደ ሰው የማይተላለፉ በሽታዎች የልብ ሕመም፣ የስኳር፣ የሳንባና የካንሰር በሽታ 38 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎችን ለሞት ዳርጓል፡፡ ከእነዚህም መሀል 16 ሚሊዮኑ ከ70 ዓመት በታች እንደሆኑ ሪፖርቱ ይጠቁማል፡፡ በየዓመቱ ሕይወቱ ከሚያልፈው 16 ሚሊዮን ውስጥ 82 በመቶ የሚሆኑት ሕዝብ የሚሞተው ደግሞ በድሃና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገሮች እንደሆነም ሪፖርቱ ይጠቁማል፡፡ ‹‹ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ይህንን ወረርሽኝ የመከላከል አቅም አለው፤›› ያሉት የዓለም አቀፉ የጤና ተቋም ኃላፊ ማርግሬት ቻን ናቸው፡፡ ኃላፊዋ የሚሊዮኖችን ሕይወት በሚቀጥሉት አሥር ዓመት ለማትረፍ 11.2 ቢሊዮን ዶላር በየዓመቱ እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል፡፡ ጥናቱ እንደሚያመለክተው የአኗኗር ስልታቸው ሞት ከሚያስከትልባቸው ሰዎች መካከል 6 ሚሊዮን የሚሆኑት በትምባሆ ሕይወታቸው ያልፋል፡፡ 3.3 ሚሊዮን ሲሆን፣ ሞት ደግሞ በአልኮል አማካይነት ይከሰታል፡፡ 3.2 ሚሊዮን የሚሆነው ሞት ሚከሰተው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ባለማድረግ ሲሆን፣ 1.7 ሚሊዮን የሚሆነው ሞት ደግሞ ብዛት ያለው ጨው በመመገብ እንደሚከሰት የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡ እንደ ሜንዲስ ገለጻ 42 ሚሊዮን የሚሆኑ ዕድሜአቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆነ ሕፃናት ከመጠን ያለፈ የስብ ክምችት ሲኖርባቸው፣ 84 በመቶ የሚሆኑ ታዳጊዎች በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አያደርጉም፡፡ ይህም የችግሩን አሳሳቢነት ከፍተኛ አድርጐታል፡፡ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከ2011 እስከ 2025 ባለው ጊዜ ውስጥ እነዚህን ጐጂ የአኗኗር ዘዬ ልማዶች ለማስቀረት ዘጠኝ ዓለም አቀፍ ግቦችን አስቀምጧል፡፡ ይህም በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ የችገሩን አንድ አራተኛ ይቀንሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ከነጥቦቹ መካከልም የትምባሆና የአልኮል ምርቶች ማስታወቂያ ላይ ዕገዳ በመጣልና ከፍተኛ የጨውና የካፊን መጠን ያላቸው ምግቦችና መጠጦች ላይ ከፍተኛ ግብር በመጣል ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ማድረግ ነው፡፡ በዚህም በአንዳንድ አገሮች ላይ አበረታች ውጤት መመዝገቡን ድርጅቱ አስገንዝቧል፡፡ ለምሳሌ ያህል በቱርክ የትምባሆ ምርት ላይ የማስታወቂያ ዕገዳ በመጣልና በጤና ላይ ስለሚኖረው አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳሰቢያ በማስነገር በ2008 በአገሪቱ የትምባሆ ተጠቃሚዎች አኃዝ ወደ 13.4 በመቶ ዝቅ ሊል ችሏል፡፡ እንዲሁም በሐንጋሪ ለጤና ጠንቅ በሆኑ ምግቦችና መጠጦች ላይ ከፍተኛ ግብር በመጣል የተጠቃሚዎቹ ቁጥር በ27 በመቶ ሊያሽቆለቁል መቻሉ ተገልጿል፡፡ በተቀሩት አገሮች የተመዘገበው ውጤት ከዕቅድ በታች ሲሆን፣ እንቅስቃሴው ካልተጠናከረ ከባድ ችግር እንደሚያስከትል ተነግሯል፡፡ ሰዎች በለጋ ዕድሜአቸው ሲታመሙና ሲሞቱ፣ ምርታማነት ይቀንሳል፡፡ እንደዚሁም ለሕክምና ከፍተኛ ወጪ ይወጣል፡፡ ይህም በአንድ አገር ዕድገት ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ከፍተኛ ሲሆን፣ ችግሩን መቅረፍ ካልተቻለ በቀጣዩ አሥርት ዓመት ከዓለም ኢኮኖሚ ሰባት ትሪሊዮን ዶላር ለችግሩ ወጪ እንደሚሆን የዓለም ድርጅት አሳውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...