Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ጥምቀት በጃንሜዳ

ትኩስ ፅሁፎች

ብዕረ ገሞራ

የጥበብ ፍላጐት ሙቀቱ ግፊቱ በአእምሮህ ጓዳ ውስጥ በከርሰ መሬቱ የእንውጣበት ትንታግ ሲያይል መወትወቱ አእምሮህ ይከፈት ገሞራው ይፈንዳ በእጅህ ብዕር ወጥቶም ይፍሰስ በቀዳዳ በወረቀቱም ላይ በመሬቷ ቆዳ የፊደሎቹ ቅርጽ ተራራ ጐድጓዳ ይደርደር በሥርዓት መልክ ይሰጥ ለመሬቷ ይነበብ ይታወቅ ይደነቅ ውበቷ ዘመናዊ ውሻ በገጠሮች መንደር ሰዎች መንገድ ሲያልፉ ውሾች አስቸግረው እየለፈለፉ ዘመናት አለፉ ከተማ ሲመጣ ዘመኑ ሲቀየር ውሻ መጮህ ትቶ ሲጀምር ማቀርቀር የውሾቹን ሥራ ሰዎቹ ዘረፉ አላሳልፍ አሉ እየተላከፉ፡፡ ሰው መሬትን ይወዳል … ካፈር ስለወጣ በምድር ይኖራል … ሚሄድበት ቢያጣ በሷም ይቀበራል … ከሥጋው ባይወጣ ካሳሁን ዓለሙ ‹‹ብዕረ ገሞራ›› 2007 ዓ.ም.

* * *

ያልበቁ ፖሊሶች

በቅርቡ ከ ዘኢንዲፔንደንት የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው በመቶዎች የሚቆጠሩ የእንግሊዝ ፖሊሶች የተሰጣቸውን አካል ብቃት ፈተና ወድቀዋል፡፡ ፈተናውን መቶ በመቶ ማለፍ የቻሉት ሁለት የፖሊስ ኃይል ተቋሞች ሀምበርባይድና ሰርቬይ ፖሊስ ብቻ ናቸው፡፡ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት የወጣው የአካል ብቃት ፈተና በተወሰነ ሰዓት ልዩነት በማሽን መሮጥ ሲሆን፣ ወደ 356 የሚሆኑ ሜትሮፖሊሶች ማለፍ ተስኗቸዋል፡፡ ከአጠቃላይ ከ9,377 ወንዶች 175ና ከ2,998 ሴቶች 239 አጥጋቢ ብቃት የላቸውም፡፡ የሜትሮፖሊታን ፖሊስ የሰው ኃይል አስተዳደር የወደቁት ራሳቸውን የሚያጐለብቱበት መንገድ እንደሚመቻች ጠቁመዋል፡፡ ፈተናው በየዓመቱ እንዲሰጥ ትዕዛዙን ያስተላለፉት የፖሊስ ኃይል ኃላፊ እ.ኤ.አ. በ2018 ከአሁኑ የበለጠ ከባድ መለኪያዎች እንደሚተገበሩ ተናግረዋል፡፡ ኦፊሰሮች የሚጠበቅባቸው መሠረታዊ ችሎታ በ15 ሜትር የማሽን ሩጫ 5.4 እስከ 5 ደረጃ መድረስ ሲሆን፣ ልዩ ኃይል፣ ታጣቂዎችና ፐብሊክ ኦርደር የገመድ ፈተና እስከ 10.5 ደረጃ ድረስ በ20 ሰከንድ ማጠቃለል ይጠበቅባቸዋል፡፡ አስገድዶ መድፈር ባያስቀጣ ኖሮ? በዩናይትድ ስቴትስ በተደረገ ጥናት 31.7 በመቶ የሚሆኑ ወጣት ወንዶች ሴትን ልጅ አስገድዶ መድፈር የሚያስከትለው ቅጣት ባይኖር ድርጊቱን ለመፈጸም ትደፍራላችሁ ወይ? ለሚል ጥያቄ የሰጡት ምላሽ እንደሚፈጽሙ የሚያሳይ ነው፡፡ ጥናቱን ያደረገው ዳኮታ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን፣ 86 ወንዶችን አሳትፎ የ73ቱን መልሶች ጥቅም ላይ አውሎታል፡፡ በቀጣይም በስፋት ለመሥራት ማቀዱን አሳውቋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው ረዳት ፕሮፌሰርና የሳይኮሎጂ መማክርት ሣራ ኤድዋርድ እንደገለጹት አስገድደው የሚደፍሩ ወንድ ተማሪዎች እንዳሉና ድርጊታቸውንም በኋላ እንደሚክዱ ተናግረዋል፡፡ ባለቤቷ ላይ በስህተት የተኮሰችው ሚስት በሰሜን ካሮላይና ፎርት ብራግ በተሰኘ ግዛት ውስጥ የሚኖረው ወታደር ባለቤቱ በተኮሰችው ጥይት መመታቱ ተዘገበ፡፡ የ28 ዓመቱ ዚያ ሴጉሌ ሚስቱን ለማስገረም በማሰብ ደህና ዋይ ብሏት ከወጣ በኋላ ድንገት ተመለሰ፡፡ የቤቱን መጥሪያም ተጫነ፡፡ ለማስገረም ብሎ ወደ ቤቱ የተመለሰው ዚያ ሴጉሌ ግን ሁኔታዎች ድንገት ተቀየሩበት፡፡ የደኅንነት ሥጋት ባለበት አካባቢ የምትኖረው ባለቤቱ የመጥሪያውን ድምፅ ስትሰማ ዘራፊ እንደገባ ነበር የጠረጠረችው፡፡ ስለዚህም መሣሪያዋን በፍጥነት አቀባብላ ቃታውን ሳበች፡፡ በኬፕ ፈር ቫሊ ሜዲካል ሴንተር አስፈላጊው ሕክምና ከተደረገለት በኋላ ‹‹ደህናነኝ›› በማለት ወደ ቤቱ ተመልሷል፡፡ ፖሊስ በባለቤቱ ላይ ባደረገው ምርምራም በተለያዩ ጊዜያት ባጋጠማት የዘራፊዎች ቤት ሰብሮ የመግባት ሁኔታ በፈጠረባት ሥጋት የተከሰተመሆኑን አብራርታለች፡፡ ጆሴ ኤስት ሬላ የተባለ ጎረቤታቸው በአካባቢው አለ ስለተባለው አለመረጋጋት ተጠይቆ በሰጠው ምላሽም ‹‹በአካባቢው ብዙ ጉዳት የሚያደርሱ ሰዎች አሉ፡፡ ስለዚህም ሁላችንም እንሰጋለን፡፡ ሥጋቱ የሚያይለው ደግሞ በሴቶች ላይ ነው፡፡ በመሆኑም ራስህን ለመጠበቅ ማድረግ ያለብህን ማንኛውንም ነገር ታደርጋለህ›› ብሏል፡፡ እሱ እንደሚለው በአካባቢው ከፍተኛ አለመረጋጋት ይታያል ‹‹እኔ ራሴ ድንገት ሌሊት ብንን ብዬ መሣሪያ ባልተኩስም ማነው ብዬ እጮሀለሁ›› ሲል በአካባቢው ስለሚታየው ያለመረጋጋት ለአሶሼትድ ፕረስ ገልጿል፡፡

* * *

በእንግሊዝ ከሴቶች ግርዛት ጋር በተያያዘ የመጀመሪያው ችሎት ተካሄደ

በለንደን የሴት ልጅ ግርዛት በመፈጸም የተከሰሰው ዶክተር የፍርድ ቤት ውሎ በአገሪቱ ተመሳሳይ ኬዝ ከዚህ በፊት ፍርድ ቤት ቀርቦ ባለማወቁ የመጀመሪያው መሆኑ ተዘግቧል፡፡ እ.ኤ.አ. 2012 ላይ በሆስፒታሉ የወለደች እናትን የገረዘው የ32 ዓመቱ ዳኑሶን ዳርማሴና ላይ ክስ የተመሠረተው የሴት ልጅ ግርዛትን በሚቃወሙ ቡድኖች ግፊት ነው፡፡ በወቅቱ የ24 ዓመት ወጣት የነበረችው ሴት መጀመሪያ ግርዛት የተፈጸመባት ሶማሊያ ውስጥ የስድስት ዓመት ሕፃን ሳለች ነበር፡፡ ወሊድ ላይ በምጥ ምክንያት ችግር ሲፈጠር ደግሞ ሐኪሙ ዳርማሴና መፍትሔ ነው ብሎ በማመን ለሁለተኛ ጊዜ ገርዟታል፡፡ በግርዛቱ ወቅት በአስተርጓሚነት የረዳ ሐሰን መሐመድ የተባለ የ41 ዓመት ግለሰብም በተባባሪነት ተከስሷል፡፡ በተመሠረተበት ክስ ጥፋተኛ መሆኑን የካደው ዳርማሴና የተፈጠረው ነገር ከሕክምና ሙያ አንፃር ተቀባይነት የሚኖረው እንደሆነ ለማስረዳት ሞክሯል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ100 እስከ 140 ሚሊዮን የሚሆኑ ሴቶችና ልጃገረዶች ግርዛት እንደተፈጸመባቸው ሪፖርቶች ያሳያሉ፡፡ እ.ኤ.አ. ከ1985 ጀምሮ በእንግሊዝ የሴት ልጅ ግርዛት በሕግ የተከለከለ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ግን ማንም ወንጀሉን በመፈጸም ተከስሶ እንደማያውቅ ዘገባው ያሳያል፡፡

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች