Monday, March 4, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናአንድነት ፓርቲ የምርጫ ቦርድን ትዕዛዝ አልቀበልም አለ

አንድነት ፓርቲ የምርጫ ቦርድን ትዕዛዝ አልቀበልም አለ

ቀን:

ጥር 5 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አማካይነት በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ጠቅላላ ጉባዔውን እንዲጠራ የታዘዘው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)፣ ጠቅላላ ጉባዔ ጥራ መባሉ ሕገወጥ በመሆኑ ጠቅላላ ጉባዔ እንደማይጠራ አስታወቀ፡፡ የፓርቲው ተጠባባቂ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አስራት አብርሃ፣ የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት ጥር 9 ቀን 2007 ዓ.ም. ተሰብስቦ እንደነበር አስታውሰው፣ ‹‹በዚህ ዕለት ምርጫ ቦርድ ለፓርቲው የላከው ደብዳቤ እንዲነበብ ተደርጎ ፈጽሞ ሕገወጥ እንደሆነ ውሳኔ አሳልፏል፤›› በማለት ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የአንድነት ፓርቲን ጠቅላላ ጉባዔ የመጥራት ኃላፊነት ያለበት የፓርቲው ብሔራዊ ምክር ቤት ወይም ደግሞ በፓርቲው አንድ ሦስተኛ አባላት ጥያቄ መሠረት መሆኑ እየታወቀ፣ በ15 ቀናት ውስጥ ጠቅላላ ጉባዔ ጥሩ የሚለው የቦርዱ ትዕዛዝ አንድነትን ከጨዋታ ለማስወጣት ያለመ ነው በማለት ፓርቲው ትዕዛዙን መቃወሙን አስታውቀዋል፡፡ የቦርዱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደምሰው በንቲ ‹‹ቦርዱ ባስቀመጠው የጊዜ ገደብ መሠረት ፓርቲዎቹ (አንድነትና መኢአድ) ችግሮቻቸውን ፈተው ይመጣሉ በሚል እየጠበቀ ነው፡፡ ከዚህ ውጪ የምንለው ምንም ነገር የለም፤›› በማለት ለሪፖርተር ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ አቶ አስራት በበኩላቸው፣ ‹‹ሌላው ሕገወጥ ነገር አንድነት ፓርቲ አንድ አመራር ነው ያለው፡፡ አንድ አንድነት ነው ያለው፡፡ ከዚህ በተለየ ሁኔታ ሁለት አንድነት ነው ያለው በማለት ለሌለ ቡድን ዕውቅና ለመስጠት በጋራ ጠቅላላ ጉባዔ ጥሩ የሚልበት ምንም ዓይነት የሕግ ማዕቀፍ የለውም፤›› በማለት ምርጫ ቦርድን ኮንነዋል፡፡ በመሆኑም የጋራ ጉባዔ የሚባል ነገር የለም ያሉት አቶ አስራት፣ አንድነት የሚጠራው የጋራ ጉባዔ አይኖርም በማለት በምርጫ ቦርድ የተሰጠውን ትዕዛዝ ፓርቲው እንዳልተቀበለው አስረድተዋል፡፡ ፓርቲው ጥር 8 ቀን 2007 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ የቦርዱን ውሳኔ፣ ‹‹በማን አለብኝ ስሜት የተሰጠ ውሳኔ ሳይታረም ቢቀርና ገዢው ፓርቲ ያለምንም ጠንካራ ተቀናቃኝ ብቻውን ሮጦ ብቻውን እንዲያሸንፍ የሚያደርግ ተቋማዊ ሴራ ቦርዱን በታሪክ ተጠያቂ በማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ በዚህ አገር ዘላቂ ሰላም ላይ ለሚፈጠረው አደጋ ቦርዱ ከተጠያቂነት አይድንም፤›› በማለት አስታውቋል፡፡ አንድነት ፓርቲ የዘንድሮውን ምርጫ በሁሉም ሒደቶች ሕዝቡን በማሳተፍ ለመወዳደር ቢያቅድም፣ ገዢው ፓርቲ በምርጫ ቦርድ በኩል ከፍተኛ እንቅፋት እየፈጠረበት እንደሆነ የጠቀሱት አቶ አስራት፣ በዚህም ምክንያት ይህንኑ ጉዳይ ለሕዝቡ ለማሳወቅ በመጪው እሑድ ፓርቲው ሕዝባዊ ሠልፍ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...