Friday, December 9, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየአካል ጉዳተኞችን የመረጃ ተደራሽነት ችግር ለመቅረፍ የሚዲያ ፎረም ተቋቋመ

  የአካል ጉዳተኞችን የመረጃ ተደራሽነት ችግር ለመቅረፍ የሚዲያ ፎረም ተቋቋመ

  ቀን:

  የአካል ጉዳተኞችን የሚዲያ ተጠቃሚነትና ተደራሽነት ችግር ለመፍታት የሚያስችል የአካል ጉዳተኞች የሚዲያ ፎረም ጥር 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ተቋቋመ፡፡ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እንዲሁም የሚዲያና የአካል ጉዳተኞች ማኅበራት ተወካዮችን ባሳተፈ መልኩ የተቋቋመው ይኸው ፎረም የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የመረጠ ሲሆን፣ ኮሚቴውን በጥምረት የሚመሩት ደግሞ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለሥልጣን ናቸው፡፡ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በአገር ደረጃ አካል ጉዳተኞች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማስተባበር፣ አቀናጅቶ የመሥራት እንዲሁም መረጃ በማቅረብ ረገድ የበኩሉን ድጋፍና አስተዋጽኦ የሚያደርግ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለሥልጣን ደግሞ የሚዲያ ተቋማቱ ለአካል ጉዳተኞች ምን ያህል ተደራሽ ናቸው የሚለውንና የመረጃ ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጥ ይሆናል፡፡ አቶ ፈለቀ ጀምበር የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማኅበራዊ ደህንነት ልማት ማስፋፊያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር፣ አካል ጉዳተኞች የመረጃ ተደራሽነት ችግር እንዳለባቸው ገልጸው፣ ችግሩን ለማቃለል ሚዲያ ተቋማት ላይ ትልቅ ኃላፊነትና ተግባር ተጥሎባቸዋል፣ ስለዚህ አካል ጉዳተኞች የማኅበራዊና የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሁሉም የሚዲያ ተቋማት ለቆሙለት ዓላማ ተፈጻሚነት ሲሠሩ የአካል ጉዳተኞችን ጉዳይ እንዲያካትቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ አቶ ዴረሳ ተረፈ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለሥልጣን የመገናኛ ብዙኃን ክትትል፣ አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር፣ በመንግሥትና በግል የሚዲያ ተቋማት ዘንድ የአካል ጉዳተኞችን ጉዳይ ተደራሽ ለማድረግ የተወሰኑ ጅምሮች ቢኖሩም ክፍተት እንዳለው፣ በሳምንት አንድ ጊዜ በኢትዮጵያ ሬዲዮ የሚተላለፈውም የብሩህ ተስፋ ፕሮግራም በስፖንሰር ሲደገፍ እንደቆየ ሆኖም የአካል ጉዳተኞች ጉዳይ በስፖንሰር ላይ ብቻ የተመረኮዘ መሆን እንደሌለበት ገልጸዋል፡፡ አካል ጉዳተኞች ከሚዲያው ተጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚገባና አካል ጉዳተኞችን ተደራሽ ለማድረግ በተለይ የመንግሥት ሚዲያ በሕገ መንግሥቱና በሌሎችም ሕጎች ዘንድ ተጠያቂነት፣ የግል ሚዲያ ተቋማት ደግሞ ማኅበራዊ ኃላፊነት እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው ጭፍጨፋና ሥጋቱ

  ኦሮሚያ ክልል ከቀውስ አዙሪት መላቀቅ ያቃተው ይመስላል፡፡ ከ200 በላይ...

  እናት ባንክ ካፒታሉን ወደ አምስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ወሰነ

  መጠባበቂያን ሳይጨምር የባንኩ የተጣራ ትረፍ 182 ሚሊዮን ብር ሆኗል እናት...

  ቡና ባንክ ዓመታዊ ትርፉን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ማሻገር ቻለ

  ቡና ባንክ በ2014 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔውን ለመጀመርያ...