Tuesday, November 28, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ለዘንድሮ የመንግሥት በጀት ጉድለት ማሟያ ብር እንደማያትም ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ

ተዛማጅ ፅሁፎች

መንግሥት የዘንድሮ በጀት ጉድለቱን ለመሸፈን የሚያስፈልገውን ብር በቀጥታ ብድር ከብሔራዊ ባንክ እንዲያገኝ እንደማይደረግ፣ የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዥ አቶ ተክለ ወልድ አጥናፉ አስታወቁ፡፡ ዋና ገዥው ይህንን የገለጹት ሰኞ ጥቅምት 27 ቀን 2010 ዓ.ም. በፓርላማ ለበጀትና ለፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡት ሪፖርት ነው፡፡

ከብሔራዊ ባንክ የሚገኝ ቀጥታ ብድር ወይም ‹‹ብር ማተም›› መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በመሆኑም የበጀት ጉድለቱን ለመሸፈን የሚቻልበትን ሥሌት በአሁኑ ወቅት ብሔራዊ ባንክ እያከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከውጭ ብድር የበጀት ጉድለቱን መሸፈን የዋጋ ግሽበት የሚያስከትል መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ የብር ምንዛሪ ተመን እንዲቀንስ ተወስኖ ተግባራዊ መደረግ በጀመረበት ወቅት ይህንን መፍቀድ የሚያስከትለውን የዋጋ ንረት እጥፍ ያደርገዋል፡፡ በመሆኑም በዚህ መንገድ የበጀት ጉድለቱ እንደማይሸፈንና በተቻለ አቅም የበጀት ጉድለቱን ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው በመሰብሰብ ለመሸፈን ጥረት እንደሚደረግ አቶ ተክለ ወልድ አስረድተዋል፡፡

ይህንን ዕውን ለማድረግ ተግባራዊ የሚደረገው የሚታወቅ መሣሪያ የመንግሥት የግምጃ ቤት ሰነድ ሽያጭ ሲሆን፣ በ2010 ዓ.ም. ተግባራዊ መደረግ የሚጀምረው የሁለተኛ ገበያ የዕዳ ሰነድ ሽያጭ (Secondary Market)፣ ሌላው አኮኖሚው የሚያመነጨውን ገንዘብ ሰብስቦ ለበጀት ጉድለት መሸፈኛ የሚውልበት ሥልት እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

የ2010 ዓ.ም. የመንግሥት አጠቃላይ በጀት 320.8 ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ የበጀት ገድለቱ 53 ቢሊዮን ብር ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች