Sunday, April 2, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ሁለት ኩባንያዎች 400 ሺሕ ቶን ስንዴ ለማቅረብ ጨረታ አሸነፉ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

400 ሺሕ ቶን ስንዴ ለመግዛት የወጣውን ጨረታ ፕሮሚሲንግ ኢንተርናሽናልና ኢንትሬድ የተባሉ ሁለት ኩባንያዎች በ3.3 ቢሊዮን ብር የመጫረቻ ዋጋ አሸነፉ፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት የተከፈተው ጨረታ ስድስት ዓለም አቀፍ የስንዴ አቅራቢዎች እንደተሳተፉበት ይታወሳል፡፡

በሦስት ሎቶች ተከፍፍሎ በወጣው ጨረታ ማለትም ሎት አንድ 200 ሺሕ ቶን፣ ሎት ሁለትና ሦስት እያንዳንዳቸው 100 ሺሕ ቶን እንዲይዙ ተደርጎ ጨረታው ወጥቷል፡፡

በዚህም መሠረት ለመጀመርያው ሎት (200 ሺሕ ቶን) ስንዴ አነስተኛውን የመጫረቻ ዋጋ የሰጠው ፕሮሚሲንግ በ1.64 ቢሊዮን ብር ሊያሸንፍ ችሏል፡፡  

በሌላ በኩል ኢንትሬድ ለሎት ሁለትና ሦስት ለእያንዳንዳቸው 830.9 ሚሊዮን ብርና 824.8 ሚሊዮን ብር ዝቅተኛ የመጫረቻ ዋጋ በማቅረብ፣ ሁለቱንም ሎቶች አሸንፏል፡፡

ለሁለቱም ኩባንያዎች አሸናፊነታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ እንደተሰጣቸው፣ ግዥውን ያከናወነው የመንግሥት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ድርጅት የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አሰፋ ሰሎሞን ለሪፖርተር አረጋግጠዋል፡፡

በቀጣዮቹ ሰባት የሥራ ቀናት ውስጥ ከተጫራቾች የሚነሱ ቅሬታዎች ካሉ የሚስተናገዱ ሲሆን፣ ምንም ዓይነት ቅሬታዎች ካልመጡ ድርጅቱ ከሁለቱም አሸናፊ ኩባንያዎች ጋር ውል ይፈጽማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በወራት ውስጥ ተገዝቶ አገር ውስጥ ይገባል ተብሎ የሚጠበቀው 400 ሺሕ ቶን ስንዴ፣ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ባለው ድርቅ ምክንያት ተረጂ ከሆኑት 8.5 ሚሊዮን ሰዎች ውስጥ 5.4 ሚሊዮን ለሚሆኑት ይውላል፡፡

ስንዴው ጂቡቲ ወደብ ከተራገፈ በኋላ አዳማ፣ ኮምቦልቻ፣ ደሴ፣ መቀሌና ድሬዳዋ የሚገኙ የእህል መጋዘኖች እንደሚጓጓዝ ታውቋል፡፡  

 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች