የሚድሮክ ግሩፕ ዓመታዊ የስፖርት ውድድር ተጀመረ
በሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ኩባንያዎችና ተጋባዥ ተቋማት መካከል የሚካሄደው ዓመታዊ ውድድር ጥር 17 ቀን 2007 ዓ.ም. በመቻሬ ሜዳ ተጀመረ፡፡
ለሦስት ወራት የሚቆየው ይህ የወዳጅነት የስፖርት ውድድር ቴክኖሎጂ ግሩፑን ኩባንያዎችን ጨምሮ ፖልሪዮስ፣ ዳሸን ባንክ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ ናሽናል ሞተርስ፣ ሞሐ ለስላሳ መጠጥ ኢንዱስትሪ፣ አዲስ ኢንተርናሽናል ካተሪንግ፣ ኒያላ ኢንሹራንስ፣ ሆራይዘን አዲስ ጎማ፣ ኢኳቶሪያ ቢዝነስ ግሩፕ፣ ኢትዮ ሌዘር ኢንዱስትሪና ሜጋ ተካፋይ ይሆናሉ፡፡
ስፖርታዊ ውድድሮች በእግር ኳስ፣ በመረብ ኳስ፣ በገመድ ጉተታ፣ በሜዳ ቴኒስ፣ በሩጫ፣ በዱላ ቅብብሎሽ፣ በጠረጴዛ ቴኒስ፣ በቼዝና በዳማ የሚካዱ ሲሆን፣ ወንዶና ሴቶች ተወዳዳሪዎችም ተካፋይ መሆናቸው ታውቋል፡፡