Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትፌዴሬሽኑ ለባህር ዳር ስታዲየም ከፊፋ ዕውቅና ሊጠይቅ ነው

ፌዴሬሽኑ ለባህር ዳር ስታዲየም ከፊፋ ዕውቅና ሊጠይቅ ነው

ቀን:

በብቸኝነት አህጉራዊውም ሆነ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን በማስተናገድ ከሚታወቀው የአዲስ አበባ ስታዲየም በተጨማሪ፣ በመጠናቀቅ ላይ ያለው አዲሱ የባህር ዳር ስታዲየም በዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ዕውቅና ማግኘት ይችል ዘንድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለፊፋ ጥያቄ ሊያቀርብ መሆኑ ተሰማ፡፡ አዲሱ የባህር ዳር ስታዲየም ዕውቅና ከተሰጠው በውድድር ዓመቱ ኢትዮጵያን በመወከል በአፍሪካ የክለቦች ሻምፒዮናና ለአፍሪካ ክለቦች ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የሚሳተፉት ቅዱስ ጊዮርጊስና ደደቢት እግር ኳስ ክለቦች በሜዳቸው የሚያደርጉት ጨዋታ ይስተናገድበታል ተብሎ እንደሚጠበቅ የፌዴሬሽን ምንጮ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ የዓለም አቀፍ ደረጃን ጠብቆ እንደተገነባ የሚነገርለት ሁለገቡ የባህር ዳር ስታዲየም፣ አራተኛውን የመላ ኢትዮጵያ ጨዋታዎችን በአጥጋቢ ሁኔታ ከማስተናገዱ ሌላ ከብሔራዊ ሊግ ወደ ፕሪሚየር ሊግ የሚያድጉ ሁለት ክለቦችን ለመለየት፣ በ16 የብሔራዊ ሊግ ክለቦች መካከል የተደረገው ጨዋታም መካሄዱ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...