Friday, June 9, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልምን የት?

ምን የት?

ቀን:

የኪሮስ ዓለማየሁ የሕይወት ታሪክ ዓርብ ይመረቃል

በዝነኛው የትግርኛ ሙዚቃ ድምፃዊ ኪሮስ ዓለማየሁ የሕይወት ታሪክ ላይ ያተኮረ መጽሐፍ ዓርብ ጥር 22 ቀን 2007 ዓ.ም. በአክሱም ሆቴል ይመረቃል፡፡ ‹‹ኪሮስ ዓለማየሁ ከ1944 እስከ 1986›› የተሰኘው ይኼው መጽሐፍ የተጻፈው በሰሎሞን ገብረእግዚአብሔር ሲሆን፣ ስለ ኪሮስ የሙዚቃ ሕይወትና የዘፈኖቹ ይዘት  ያትታል፡፡

በምርቃቱ ላይ የኪሮስ ልጅ ድምፃዊት ዛፉ ኪሮስና አብርሃም ገብረመድህንን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ የትግርኛ ዘፋኞች የሚገኙ ሲሆን፣ ከኪሮስ ዘፈኖች የተመረጡትን ያቀነቅናሉ፡፡

‹‹አንጉዐይ ፍስስ››፣ ‹‹ምቕናይ››፣ ‹‹ትግራይ አደይ›› በሚባሉ ዘፈኖቹ የበለጠ የሚታወቀውቅ ኪሮስ፣ አብዛኛው ዘፈኖቹ ቅኔያዊና ፖለቲካዊ ይዘት እንዳላቸው ይነገራል፡፡ ስድስት አልበሞች ያሉት ኪሮስ ከ1973 እስከ 1976 ዓ.ም. በራስ ቴአትር ሠርቷል፡፡ በ1970ዎቹ አጋማሽ ለሦስት ዓመት በአዲስ አበባ ማዕከላዊ እስር ቤት ታስሮ የነበረው ኪሮስ ሕልፈት መንስዔ በትክክል ባለመታወቁ በርካታ መላ ምቶች ቢኖሩም፣ ተመርዞ እንደሞተ የሕክምና ባለሙያዎች አረጋግጠዋል፡፡ በማን እንደተመረዘ ባለመታወቁ አወዛጋቢውን የኪሮስ አሟሟት ጸሐፊው እንቆቅልሽ ብሎ በመጽሐፉ አስፍሯል፡፡ 

******

ዐውደ ርዕይ

‹‹ሥዕላዊ ስላቅና ሥዕላዊ ምፀት የተሰኘ የፖርትሬት አርት ዐውደ ርዕይ ዓርብ ጥር 22 ቀን 2007 ዓ.ም. በጋለሪአ ቶሞካ ይከፈታል፡፡ በዐውደ ርዕዩ የሠዓሊ ቴድሮስ መስፍን (ሬዲ ማን) 30 ፖርትሬቶች ለዕይታ ይቀርባሉ፡፡ ሥዕሎቹ ታዋቂ የአገር ውስጥና የውጪ አገር ሰዎችን የሚያሳዩ ሲሆን፣ ለሁለት ወራት ለሕዝብ ዕይታ ክፍት ይሆናል፡፡ በሠዓሊው ሥራዎች ላይ ያተኮረ ውይይት የካቲት 22 ቀን 2007 ዓ.ም. ከረፋዱ 4 ሰዓት ጀምሮ በጋለሪው ይካሄዳል፡፡

******

‹‹ሮዛ››

‹‹ሮዛ›› የተሰኘው መጽሐፍ ቁጥር ሁለት ዕትም ገበያ ላይ ውሏል፡፡ ሮዛ ይድነቃቸው በምትባል ሴተኛ አዳሪ ሕይወት ላይ ያተኮረው መጽሐፍ 15 ንዑስ ክፍሎች አሉት፡፡ መጽሐፉን ያዘጋጀው አርታኢ ፍፁም ብርሃኔ አራጌ በመግቢያው እንደገለጸው፣ መጽሐፉ ከባለታሪኳ የውሎ ማስታወሻ የተሰበሰበ ነው፡፡ 191 ገጽ ያለው መጽሐፉ በ50 ብር ከ65 ሳንቲም ይሸጣል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ