Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊእስራኤላዊው ምሁር በፋሽስት ወረራ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ የሚያጠና ተቋም መቋቋም አለበት አሉ

እስራኤላዊው ምሁር በፋሽስት ወረራ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ የሚያጠና ተቋም መቋቋም አለበት አሉ

ቀን:

የአሽዊትዝ ማጎሪያ ካምፕ ነፃ የወጣበትን 70ኛ ዓመት በማስመልከት በኢትዮጵያ የጀርመንና የእስራኤል ኤምባሲዎች በአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አዳራሽ ባለፈው ሐሙስ ባዘጋጁት የሆሎኮስት መታሰቢያ መድረክ ላይ የተገኙት እስራኤላዊው የሆሎኮስት ጥናት ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሮበርት ሮዜት፣ ኢትዮጵያ በፋሽስት ኢጣሊያ የተፈጸመባትን ጭፍጨፋ የሚያጠና ተቋም መመሥረት እንደሚገባት አሳሰቡ፡፡

ፕሮፌሰሩ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በዓለም ላይ የተፈጸመው ኢፍትሐዊ የጅምላ ጭፍጨፋ በሙሉ እኩል በመሆኑ፣ አይሁዶች በናዚ ጀርመን የተፈጸመባቸውን ወደር የማይገኝለት የ20ኛው ክፍለ ዘመን ግድያ ከሌሎቹ ለይቶ ማየት አይቻልም፡፡ ከናዚ በፊትም ሆነ በኋላ ሌሎች የጅምላ ጭፍጨፋና የዘር ማጥፋት ወንጀሎች መኖራቸውን ያወሱት በኢየሩሳሌም የአይሁድ ጥናት ማዕከልና ወመዘክር ዳይሬክተሩ፣ የኢትዮጵያም ታሪክ መጠናትና በስፋት መታወቅ እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡ ‹‹እኔ በበኩሌ በጣም ኢምንት ዕውቀት ብቻ ነው ያለኝ፤›› ያሉት ፕሮፌሰሩ፣ ይህ የቤኒቶ ሙሶሎኒ ጭፍጨፋ ለምን፣ እንዴትና ምንስ እንደተከሰተበት በዝርዝር ሊታወቅ እንደሚገባው ተናግረዋል፡፡

በዓለም ላይ ከተከሰቱት እጅግ አሰቃቂ የሰው ለሰው እልቂቶች ውስጥ ከፍተኛው እንደሆነ በሚነገርለት ናዚዎች በአይሁዶች ላይ ያደረሱት የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ፣ ከስድስት ሚሊዮን በላይ አይሁዶች በጅምላ መገደላቸውን የሚያስታውሱት ፕሮፌሰሩ፣ ከዚያ በኋላም በተለያዩ አገሮች ይህ መሰሉ ጥፋት መቀጠሉናን፣ ሰዎች ከዚህ ተምረው ድጋሚ ወደዚህ መሰሉ አሳዛኝ ታሪክ እንዳይገቡ ማስተማር የሚቻለው መጀመሪያ ምን እንደተፈጠረና ለምን እንደተደረገ ማጥናት ሲቻል በመሆኑ፣ የጥናት ማዕከላቱ መቋቋም አስፈላጊ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡

- Advertisement -

ከሁለት አሥርት ዓመታት በፊት በሩዋንዳ ከዚያም በዳርፉር፣ ቀደም ሲልም በካምቦዲያ የታዩት የዘር ማጥፋቶችን ጨምሮ ዛሬም በሶሪያና በሌሎች አካባቢዎች እየታየ የሚገኘው የእርስ በርስ እልቂት ከሆሎኮስት ጋር እኩል መታየት እንደሚገባውም አስረድተዋል፡፡

ሁለቱ አገሮች ትናንት የተፈጠረውን የማይረሳ ታሪክ ወደጎን ትተው ላለፉት አሥርት ዓመታት በጋራ ለመማማርና ለመሥራት ጥረት የሚያደርጉት፣ የተፈጠረውን አሳዛኝ ታሪክ በውል በመመርመር እንደሆነም ፕሮፌሰሩና በዕለቱ በጀርመን መንግሥት ተወክለው ንግግር ያደረጉት ሚስተር ፌሊክስ ክሌይን በጋራ ገልጸዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እ.ኤ.አ. በ2005 ኅዳር ወር ባፀደቀው አዋጅ መሠረት በየዓመቱ ጥር 20 ቀን ታስቦ የሚውለው የሆሎኮስት መታሰቢያ፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ሲካሄድ ስድስት ሚሊዮኑን አይሁዳውያን ሰለባዎችን ለማስታወስ ስድስት ሻማዎችን የእስራኤልና የጀርመን ተወካዮች ለኩሰዋል፡፡ ከእነዚህም መካከል በኢትዮጵያ የእስራእል አምባሳደር ወ/ሮ በላይነሽ ዜባድያና የጀርመኑ አቻቸው ሚስተር ዮአኪም ሽምዲት ይገኙበታል፡፡ በፖላንድ የሚገኘውን የአሽዊትዝ ማጎሪያ ካምፕ ከዛሬ 70 ዓመት በፊት የሶቭየት ኅብረት ወታደሮች ነፃ እንዳወጡት ይታወሳል፡፡     

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...