Wednesday, February 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአዲስ አበባ አስተዳደር ሁለተኛውን የአምስት ዓመት ዕቅድ ማዘጋጀት ጀመረ

የአዲስ አበባ አስተዳደር ሁለተኛውን የአምስት ዓመት ዕቅድ ማዘጋጀት ጀመረ

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለተኛውን የአምስት ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ማዘጋጀት ጀመረ፡፡ አስተዳደሩ ዕቅዱን የመንደፍ ኃላፊነቱን ለከተማው ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሰጥቷል፡፡

ፋይናንስ ቢሮ ይህንን ዕቅድ የሚያመነጨው ከከተማው አስተዳደር የተለያዩ ቢሮዎች ከተውጣጡ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር መሆኑ ታውቋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ጉዳዮችና ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸው ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ መነሻ ፕሮግራሞችን ካቀረበ በኋላ የአስተዳደሩ ካቢኔ ተወያይቶ፣ ዕቅዱ መያዝ ያለበትን ፕሮግራም ይወስናል፡፡

መረጃዎች እንደጠቆሙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚያዘጋጀው ዕቅድ፣ የፌዴራል መንግሥት ባስቀመጣቸው ስምንት መነሻ መዋቅራዊ ሐሳቦች ላይ ተመሥርቶ ነው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

አስተዳደሩ ይህንን መነሻ  በማድረግ የከተማው አስተዳደር ሊያካትት የሚገባውን ሐሳብ በመጨመር እንደሚያወጣ አቶ አሰግድ ገልጸዋል፡፡ ይህ ዕቅድ ፀድቆ የከተማው ገዢ ዕቅድ ሆኖ ከመውጣቱ በፊት፣ የከተማው ነዋሪዎች እንደሚወያዩበት መረጃዎች አመልክተዋል፡፡

አሁን በሥራ ላይ ያለው የአዲስ አበባ የአምስት ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በግንባታ በኩል ለመንገድ፣ ለንፁህ መጠጥ ውኃ፣ ለፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮችና ለመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ትኩረት ሰጥቷል፡፡

በሌላ በኩልም መልካም አስተዳደር ለማስፈንና የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያዎችን ለማካሄድ ትኩረት መስጠቱ ይታወቃል፡፡ እንዲዘጋጅ በተወሰነው ሁለተኛው የአምስት ዓመት ዕቅድ በተመሳሳይ ለመኖሪያ ቤቶች፣ ለንፁህ መጠጥ ውኃና ለዋና ዋና መንገዶች ግንባታ ትኩረት እንደሚሰጥ የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡

የከተማው ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ምንጮች አገላለጽ ለሁለተኛው የአምስት ዓመት ዕቅድ እንደ ሥጋት የሚታየው የፋይናንስ ፍሰት ነው፡፡ ምንጮች እንደሚሉት የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ውክልና ወስዶ የከተማው ገቢ መሰብሰብ ከጀመረ በኋላ የከተማው ገቢ ዕድገት እያሳየ መጥቷል፡፡ ነገር ግን ከተማው ውዝፍ የመኖሪያ ቤት፣ የመጠጥ ውኃ፣ የትራንስፖርት አውታርና ሌሎች ማኅበራዊ ተቋማት ግንባታዎችን ማካሄድ የሚጠበቅበት በመሆኑ ገቢው ከፍተኛ ነው ሊባል እንደማይቻል መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

‹‹ተጨማሪ ገቢ ሊኖር ይገባል›› በማለት የከተማው ገቢና የአገልግሎት ፍላጎት ተመጣጣኝ እንዳልሆነ ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ በዚህ ዓመት አስተዳደሩ 21 ቢሊዮን ብር ለማግኘት አቅዷል፡፡ ነገር ግን አስተዳደሩ ሊያከናውን የሚገባቸው ፕሮጀክቶች ከ40 ቢሊዮን ብር በላይ ሊፈጁ እንደሚችሉ ባለሙያዎቹ ይናገራሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...