በኮንጎ ብራዛቢል ለሚዘጋጀው የመላው አፍሪካ ጨዋታ የሚጫወቱ 23 ተጫዋቾችን ለመለየት ዝግጅት ማጠናቀቁን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ግንኙነት ኃላፊ አቶ ወንድምኩን አላዩ ለሪፖርተር በላኩት መረጃ ማወቅ ተችሏል፡፡
በዚህ 20 አገሮች በሚሳተፉበትና መጋቢት ወር ላይ በሚጀምረው ውድድር 20 ቡድኖች የሚሳተፉ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ የመጀመርያ ጨዋታዋን ከሱዳን ጋር ስታደርግ በደርሶ መልሱም እዚህ አዲስ አበባ ላይ እንደሚሆንም መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
ፖርቹጋላዊው አሠልጣኝ ማርያ ባሬቶ ከክልልና ክለብ የተወጣጡ ባጠቃላይ 43 ተጨዋቾችን የመረጡ ሲሆን፣ የፊታችን ዓርብ ልምምድ እንደሚያደርጉና 23ቱን ተጨዋቾች እንደሚለዩም ይጠበቃል፡፡ በመጨረሻም የሱዳንና ኢትዮጵያ አሸናፊ ከደቡብ አፍሪካ ጋር እንደሚጫወቱ ታውቋል፡፡
- Advertisement -
ለመላው አፍሪካ ጨዋታ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 23 ተጨዋቾችን ሊለይ ነው
- Advertisement -