‹‹ክርስቲያኖ ሮናልዶን የመሰለ ተጫዋች የትም ማግኘት ስለማይቻል ከሁለት ቢሊዮን ዶላር በላይ ያወጣል፡፡ በማንኛውም ምክንያት ክለቡ (ሪያል ማድሪድ) ነገ በ300 ሚሊዮን ዶላር ሊሸጠው ቢያስብ ደግሞ አንድ ሰው [ክለብ] ከፍሎ ይወስደዋል፡፡››
ይህንን የተናገሩት የዝነኛው የእግር ኳስ ተጫዋቾች ክርስቲያኖ ሮናልዶ ኤጀንት (ወኪል) ጆርጊ ሜንዴስ ናቸው፡፡ ወኪሉ እንዳሉት ሮናልዶ የዓለማችን ምርጡ ተጫዋች ነው፡፡ ‹‹ከማንም ጋር የምታነፃፅረው አይደለም፤›› ያሉት ሜንዴስ፣ አጠቃላይ የግዥ ስምምነቱ አንድ ቢሊዮን ፓውንድ ስተርሊንግ (2.03 ቢሊየን ዶላር) ይሆናል፤›› ብለዋል፡፡ ያም ሆኖ ግን ፖርቹጋላዊው ሜንዴስ የአገራቸው ልጅ ሪያል ማድሪድን አይለቅም ብለው፣ የተጫዋችነት ዘመኑን እዚያው ያጠናቅቃል ሲሉ አስታውቀዋል፡፡ በምሥሉ ላይ ዘንድሮ ለሦስተኛ ጊዜ የዓለም ምርጥ ተጫዋች ሽልማት (ባሎን ዶር) የተሸለመው ሮናልዶ ይታያል፡፡