Sunday, April 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልዳሽን ቢራ ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎች 450,000 ብር ሸለመ

ዳሽን ቢራ ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎች 450,000 ብር ሸለመ

ቀን:

ዳሽን ቢራ አክሲዮን ማኅበር ‹‹ዳሽን አርት አዋርድስ›› በሚል ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ሽልማት ሰጠ፡፡ ሽልማቱ በግጥም እንዲሁም በሥዕልና ቅርፃ ቅርፅ ለተወዳደሩ ባለሙያዎች የተሰጠ ሲሆን፣ ከየዘርፉ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ የወጡት፣ እንደየደረጃቸው የ100,000፣ 75,000 እና 50,000 ሺሕ ብር ሽልማት አግኝተዋል፡፡ ጥር 24 ቀን 2014 ዓ.ም. በሚሊኒየም አዳራሽ የተካሄደው የሽልማት ሥነ ሥርዓት ድርጅቱ አዲሱን መለያውን ያስተዋወቀበት ነበር፡፡ መለያው በዳሽን ቢራ ጠርሙስ ላይ የዳሽን ተራራን የሚያሳይ ሥዕል በግልጽ የተቀመጠበት ነው፡፡

በግጥም ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ የወጡት ሰለሞን ሞገስ፣ ኢየሩሳሌም ነጋና መዝገበቃል አየለ ሲሆኑ፣ በሥዕልና ቅርፃ ቅርፅ ደግሞ ሠዓሊ ረዳት ፕሮፌሰር ጌታቸው ዮሴፍ፣ አንተነህ ተካና ብርቱካን ደጀኔ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ወጥተው ተሸልመዋል፡፡

በዕለቱ የአሸናፊ ገጣሚያን ሥራዎች ተደምጠዋል፤ ሥዕሎችም ለዕይታ ቀርበዋል፡፡ ከአራተኛ እስከ አሥረኛ ደረጃ ያገኙም ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡ የውድድሩ ዳኞች ከኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር፣ ከኢትዮጵያ ሠዓሊያንና ቀራፂያን ማኅበር፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጥበባት ኮሌጅና ከዜማ ብዕር ኢትዮጵያ የሴቶች የሥነ ጽሑፍ ማኅበር የተውጣጡ መምህራንና ባለሙያዎች ናቸው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የኪነ ጥበብ ዘርፉን ለመደገፍና ወጣቶችን ለማበረታታት ያለመው ሽልማት ቀጣይነት እንደሚኖረው ተገልጿል፡፡ የዳሽን ቢራ አክሲዮን ማኅበር ቦርድ ዳይሬክተር አቶ ወንድወሰን ከበደ በተለይ አማተር የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች መረበታታት አለባቸው ብለዋል፡፡

ፋብሪካው ከዚህ ቀደም የሙዚቃ አልበሞችን ስፖንሰር በማድረግና በሌላም መንገድ ኪነ ጥበቡን የሚደግፉ ሥራዎች ሠርቷል ያሉት ዳይሬክተሩ፣ ሽልማቱ እስካሁን መዘግየት እንዳልነበረበትና ለወደፊት ሌሎች ዘርፎችን አካቶ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

ከኪነ ጥበብ ዘርፍ ሥዕልና ቅርፃ ቅርፅ እና ግጥም ከተቀሩት እኩል ትኩረት ስላልተሰጣቸው ለሽልማት ተመርጠዋል ብለዋል፡፡ ሽልማቱ አደባባይ ወጥተው ሥራዎቻቸው ለሕዝብ ማድረስ ያልቻሉ ወጣት ባለሙያዎችን እንደሚያበረታታ አክለዋል፡፡

 

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ከሴራ ፖለቲካ በስተጀርባ ጥቅማቸውን የሚያስጠብቁ ኃይሎች

በመኮንን ሻውል ወልደ ጊዮርጊስ የአፄ ቴዎድሮስ መንግሥት የወደቀው ከመቅደላ በፊት...

ስለዘር ፖለቲካ

በሀብታሙ ኃይለ ጊዮርጊስ  ‹‹በቅሎዎች ዝርያችን ከአህያ ነው እያሉ ይመፃደቃሉ›› የጀርመኖች...

አማርኛ ተናጋሪዋ ሮቦት

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው የሳይንስ ሙዚየም፣ ሚያዝያ 2 ቀን...

ወዘተ

ገና! ከእናቴ ሆድ ሳለሁ፤ ጠላት ሲዝትብኝ ሰምቻለሁ። በዳዴ ዘመኔም፣ በ'ወፌ ቆመችም!'፤ አውዴ ክፉ ነበር...