Friday, September 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅየ90 ዓመቱ ሙጋቤ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ወደቁ

የ90 ዓመቱ ሙጋቤ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ወደቁ

ቀን:

የ90 ዓመቱ የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ሰሞኑን በኢትዮጵያ የተካሄደውን የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ አጠናቅቀው ወደ ሀራሬ እንደተመለሱ ከሀራሬ አውሮፕላን ማረፊያ ደረጃ እወርዳለሁ ሲሉ መውደቃቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገበ፡፡

ሙጋቤ ባለፈው ረቡዕ የወደቁት ከአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበርነትን ጋር ወደ አገራቸው መመለሳቸውን በማስመልከት በመቶዎች ለሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው ንግግር ባደረጉበት ዝግጅት ላይ ነበር፡፡

በየካቲት ወር 91ኛ ዓመታቸውን የሚይዙት ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ እንደወደቁ ወዲያው ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደመኪናቸው እንዲገቡ ተደርጓል፡፡

አገራቸው ዚምባብዌ የአፍሪካ ኅብረትን በሊቀመንበርነት እንድትመራ በመመረጧ ክብር እንደተሰማቸው የገለጹት ሙጋቤ፣ ‹‹አፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ልማት ሞተር መሆን አለበት፡፡ የአፍሪካ የልማት ሞተሮች መሆን አለብን፤›› ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሙጋቤ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ላይ የሊቀመንበርነቱን ምልክት የሆነው መዶሻና የኅብረቱን ባንዲራ ከሞሪታኒያው ፕሬዚዳንት በተቀበሉበት አጋጣሚ መዶሻው ከእጃቸው አምልጦ መውደቁ ይታወቃል፡፡

*********************

[የኢትዮጵያ መንገድ]

ሕግዋን ከወሰደ

ከልብዋ ከመስኮብ

የፍቺ ደብዳቤ ስለ ተዋዋለች

ይኸውና ዛሬ

ወንዝ ቁመናዋን መልኳን ያሳመረች

ሙሽሪት ኢትዮጵያ ላ’ሜሪካ ታጨች፡፡

በሥጋዌ ፈቃድ

ከፈቀደችው ጋር ከወደደችው ጋር አንዲት ሴት እንድትኖር

የኢትዮጵያም መንገድ

መሆኑ አይቀርም ልቧ ከፈቀደ ከአሜሪካ ጋር

ምክንያቱም

ሳያገባት ደፍሯት

ሕጓን የወሰደው መስኮብ ሞቷልና

የፍቺው ደብዳቤም

በልጆችዋ ደም በቀይ ተጽፎ እጇ ላይ አለና፡፡

  • ኤፍሬም ሥዩም ተሰማ ‹‹ተዋነይ ብሉይ የግዕዝ ቅኔያት ፍልስፍና›› (2006)

******************

የኤችአይቪ ምርመራ በስማርትፎን

የአሜሪካ ተመራማሪዎች መደበኛ ስማርትፎኖችን ለፈጣንና ቀላል የኤችአይቪና ቂጥኝ ምርመራ መሣሪያ ማድረግ የሚያስችል መንገድ ማግኘታቸው ተዘገበ፡፡ የምርመራው ውጤት በሰዓታት ሳይሆን በደቂቃዎች እንደሚደርስም ተጠቁሟል፡፡

የመጀመሪያው ጥናት ሩዋንዳ ውስጥ 96 ሴቶች ላይ የተሠራ ሲሆን ውጤቱም ሳይንስ ትራንስሌሽናል ሜዲስን ጆርናል ላይ ታትሞ ነበር፡፡

ኤክስፐርቶች እንደሚሉት ይህ ቀላል የምርመራ ዘዴ በተጨማሪም ሩቅና ገጠራማ እንዲሁም የሕክምና አገልግሎት ተደራሽነት ውስን በሆነባቸው አካባቢዎች ለሚቋቋሙ ጊዜያዊ ክሊኒኮች ዓይነተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡

በባዮሜዲካል ኢንጂነሪንግ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑትና የምርምር ቡድኑ መሪ የሆኑት ሳሙኤል ሲያ ‹‹ምርምራችን እንደሚያሳየው በሙሉ ላቦራቶሪ የሚደረገውን ምርመራ በስማርትፎን አክሰሰሪዎች በመታገዝ መሥራት ይቻላል›› ብለዋል፡፡

**************

በእንግሊዝ ከሦስት ወላጆች ልጅን መፍጠር ተቀባይነት አገኘ

አወዛጋቢውን ከሦስት ወላጆች ልጅ እንዲፈጠር የማድረግ ሳይንሳዊ ዘዴ በመፍቀድና ተቀባይነት እንዲኖረው በማድረግ እንግሊዝ በዓለም የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች፡፡

ይህ ከሦስት ሰዎች ዲኤንኤ ተወስዶ ልጅ እንዲፈጠር የማድረግ ሳይንሳዊ ዘዴ በዘር ከእናት ወደ ልጅ የሚተላለፉ ከባድ በሽታዎችን መከላከልን ያለመ ነው፡፡ ይህ ሳይንሳዊ ዘዴ በእንግሊዝ ማክሰኞ ጥር 28 ቀን 2007 ዓ.ም. በፓርላማ የፀደቀው የ382 ድምጽ እንደሆነ የአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ ያመለክታል፡፡

ዘገባው እንደሚያመለክተው በዚህ ሳይንሳዊ ዘዴ መሠረት ልጅ የሚፈጠረው ከእናት፣ ከአባትና ከሌላ ለጋሽ ሴት በሚወሰዱ ዲኤንኤዎች ይሆናል፡፡ ይኼን ሕክምና ያፀደቀው ሕግ ከየካቲት ወር አጋማሽ በኋላ በእንግሊዝ ላዕላይ የተወካዮች ምክር ቤት የይሁንታ ማረጋገጫውን እንደሚያገኝና ለከርሞም ዘዴው ተግባራዊ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡

 

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...