Monday, November 28, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናአቶ ትዕግሥቱ አወሉ የአንድነት ፓርቲን ቢሮ ተረከቡ

  አቶ ትዕግሥቱ አወሉ የአንድነት ፓርቲን ቢሮ ተረከቡ

  ቀን:

  ጥር 21 ቀን 2007 ዓ.ም. የተላለፈውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔን ተከትሎ በቦርዱ ዕውቅና የተሰጣቸው የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ፕሬዚዳንት አቶ ትዕግሥቱ አወሉ፣ የፓርቲውን ጽሕፈት ቤት መረከባቸውንና ለመጪው ምርጫ የሚረዳቸውን እንቅስቃሴ መጀመራቸውን አስታወቁ፡፡

  ‹‹የቦርዱን ውሳኔ ተከትሎ ከጥር 28 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ የፓርቲውን ጽሐፈት ቤት ተረክበን አስፈላጊውን ሥራ እየሠራን ነው፤›› በማለት አቶ ትዕግሥቱ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

  ‹‹አብዛኛው አባል በየመዋቅሩ አመራር ሰጥተነው የእኛን ውሳኔ እየተጠባበቀ ነው፤›› ብለው፣ ከአብዛኛዎቹ የፓርቲ አባላት ጋር አብረው እየሠሩ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

  አብዛኛዎቹ አባላት ወደ ሰማያዊ ፓርቲ እየገቡ ነው የሚለውን አስተያየት ክፉኛ የተቃወሙት አቶ ትዕግሥቱ፣ ‹‹የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት በግልጽ ከአንድነት የሚመጡ ሰዎችን ለመቀበል ሕጋዊ ሁኔታዎችን አመቻችተናል ማለታቸው የማስታወቂያ ሥራ ነው፤›› በማለት አሁንም የአንድነት ፓርቲ መዋቅርና አባላት በፓርቲው ውስጥ እየሠሩ ነው ብለዋል፡፡

  ይህንን የሰማያዊ ፓርቲ መግለጫ ወደፊት እንደሚፈትሹት የገለጹት አቶ ትዕግሥቱ፣ ‹‹ከአንድ ወር በፊት ከነአቶ በላይ ፍቃዱ ጋር ግንኙነት እንደነበራቸው መጠቀሱ ፓርቲው ከእነዚህ አፍራሽ ኃይሎች ጋር ሲሠራ ነበር ማለት ነው፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹ወደ ሰማያዊ ፓርቲ የገቡ ግለሰቦች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ይኼ ተፈጥሮአዊ ነው፤›› በማለት የገለጹት አቶ ትዕግሥቱ፣ አሁንም ቢሆን ግን አብዛኛዎቹ አባላት ከአንድነት ጋር መቀጠላቸውን ገልጸዋል፡፡

  ለዚህም እንደ ምክንያትነት የሚያቀርቡት ደግሞ፣ ‹‹አባሉ ጠንቅቆ ስለሚያውቃቸው እነሱን ተከትሎ የሚሄድ አይኖርም፤›› የሚል ነው፡፡  የዕጩዎች ምዝገባ በአንድ ሳምንት በመራዘሙ ምክንያት ያሉዋቸውን አባላት ለምርጫው አዘጋጅተው ወደ ምርጫው ለመግባት ዝግጅት እያደረጉ እንደሆነም ተናግረው፣ ‹‹ምን ያህል አባል አለ የሚለው ጉዳይ ጠቃሚ አይመስለኝም፤›› ብለዋል፡፡

  ‹‹ነገር ግን መዋቅሩ አለ ስንል አባሉ አለ ማለታችን ነው፡፡ በሌላ መንገድ ከመዋቅሩ እንደየፍላጐቱ መግባትና መውጣት የተለመደ ነው፡፡ አንዱ ይገባል ሌላው ይወጣል፤›› በማለት አስተያየታቸውን አጠቃለዋል፡፡

  ባለፈው ረቡዕ ዕትም በርካታ የአንድነት ፓርቲ አባላት ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡ ከዚያ ወዲህ ያሉት መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፣ የካቲት 26 ቀን 2007 ዓ.ም. የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ አባላትና አመራሮች ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸው ከተገለጸ በኋላ፣ በአዲስ አበባና በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ የፓርቲው አባላትና መዋቅሮች ሰማያዊ ፓርቲን እየተቀላቀሉ ነው፡፡ ሰማያዊ ፓርቲም የአንድነት አባላት በብዛት እየተቀላቀሉት መሆናቸውን በመግለጽ ላይ ይገኛል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በችግር የተተበተበው የሲሚንቶ አቅርቦት

  ሲሚንቶን እንደ ግብዓት ተጠቅሞ ቤት ማደስ፣ መገንባት፣ የመቃብር ሐውልት...

  ‹‹የናይል ዓባይ መንፈስ›› በሜልቦርን

  አውስትራሊያ ስሟ ሲነሳ ቀድሞ የሚመጣው በተለይ በቀደመው ዘመን የባህር...

  ‹‹ልብሴን ለእህቴ››

  ለሰው ልጅ መኖር መሠረታዊ ፍላጎት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ ልብስ...

  የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የምርመራ ውጤት እስከምን?

  በፍቅር አበበ የትምህርት ጥራትን፣ ውጤታማነትንና ሥነ ምግባርን ማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ...