Saturday, November 26, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየቃል አቀባዩ ስንብት

  የቃል አቀባዩ ስንብት

  ቀን:

  ላለፉት አምስት ዓመታት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቃባይነት ያገለገሉትና በቅርቡ በኬንያ የኢትዮጵያ ቋሚ አምባሳደርነት ሹመት ፀድቆላቸው ወደ ናይሮቢ የሚያመሩት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ የካቲት 3 ቀን 2007 ዓ.ም. የመጨረሻውን ጋዜጣዊ መግለጫቸውን በመስጠት ከጋዜጠኞች ጋር የስንብት ውይይት አድርገው ነበር፡፡ በሚዲያው ዘንድ በተባባሪነታቸውም ሆነ በተደራሽነታቸው መልካም ዝና በማትረፍ የሚመሰገኑት አምባሳደሩ፣ ሚኒስቴሩ በየወሩ በሚጠራው ወርኃዊ ጋዜጣዊ መግለጫ  ከሚዲያዎች ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንዲመሠርት አስችለውት ነበር፡፡ እሳቸው ይህን ግንኙነት በመግለጽ የሚዲያ ድርጅቶችንና ጋዜጠኞችን አመስግነው፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እሳቸውን የሚተካውን አዲሱን ቃል አቀባይ በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል፡፡ በተጨማሪም ወርኃዊውን የዲፕሎማሲ ሥራ አስመልክቶ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና በተለያዩ አገሮች መካከል የተደረጉ የዲፕሎማሲ ሥራዎችንም አብራርተዋል፡፡ በተለይ ባለፈው ወር መጨረሻ በአዲስ አበባ ከተከናወነው 24ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ በኋላ፣ በኢትዮጵያ መንግሥትና ከተለያዩ አገሮች ከመጡ መሪዎችና ዲፕሎማቶች ጋር የተደረጉ ግንኙነቶችንና ውይይቶችን በዝርዝር አስረድተዋል፡፡ ከዚህ ባሻገርም ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በጂቡቲ ሰሞኑን ባደረጉት ጉብኝት፣ በሁለቱ አገሮች መካከል በዲፕሎማሲና በሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ዘጠኝ የጋራ ስምምነቶች መፈረማቸውን፣ ተሰናባቹ ቃል አቀባይ አብራርተዋል፡፡   በምሥሉ ላይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ይታያሉ (በዮናስ አብይ)

   

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የትርፍ መጠኑን በ127 በመቶ ያሳደገው አቢሲኒያ ባንክ ካፒታሉን በ2.5 ቢሊዮን ብር እንዲያድግ ወሰነ

  የአቢሲኒያ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩ  ካፒታል በ2.5 ቢሊዮን ብር...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን 55 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ወሰነ

  የአዋሽ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ዛሬ ህዳር 17 ቀን 2015...

  ከብሔራዊ ባንክ እውቅና ያገኘው ፔይሊንክ አክሲዮን ማህበር ምሥረታውን አካሄደ

  ከገንዘብ ንክኪ ነፃ የሆነ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ለመተግበር ያቀደው...