Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበላይፕዚሽ ከተማ ከንቲባ የሚመራ የልዑካን ቡድን የአዲስ አበባ ቤቶች ግንባታ ጎበኘ

በላይፕዚሽ ከተማ ከንቲባ የሚመራ የልዑካን ቡድን የአዲስ አበባ ቤቶች ግንባታ ጎበኘ

ቀን:

የጀርመን የትምህርትና የባህል ማዕከል በሆነችው ላይፕዚሽ ከተማ ከንቲባ የሚመራ የልዑካን ቡድን አዲስ አበባ ገባ፡፡ የልዑካን ቡድኑ የካቲት 3 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለውን የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታና የቀላል ባቡር ፕሮጀክቶችን ጎብኝቷል፡፡

የልዑካን ቡድኑ ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ድሪባ ኩማ ጋር የካ አባዶ እየተገነቡ ያሉትን የኮንዶሚኒየም ቤቶች ተመልክቷል፡፡

የከንቲባ ድሪባ ረዳት አቶ ወርቁ አባተ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የላፕዚሽ ከተማ የአዲስ አበባ ከተማ እህት በመሆንዋ በብዙ መስኮች የቴክኒክ ድጋፎችን ስትሰጥ ቆይታለች፡፡

በተለይ ስድስት ኪሎ ከሚገኘው አንበሳ ግቢ አንበሶችን ወደ ፒኮክ መናፈሻ ለማዘዋወር ለተቋቋመው ፕሮጀክት፣ የላይፕዚሽ ከተማ ዋነኛ ተሳታፊ ናት፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለስድስት ኪሎ አንበሶች በየዓመቱ የሕክምና አገልግሎት ትሰጣለች፡፡

ላይፕዚሽ ከተማ በዱር እንስሳት ማቆያ የምትታወቅና ብዙ ልምድ ያላት በመሆኑ፣ የፒኮክ መናፈሻ ለአንበሶች መኖሪያ እንዲሆን ሲታሰብ ዋነኛ ተዋናይ በመሆን ፕላኑን ሠርታለች፡፡

ይህንን የቴክኒክ ድጋፍ ከፍ በማድረግ ላይፕዚሽ ከተማ በቤቶችና በከተማ ባቡር ዘርፍ ያላትን ተሞክሮ ለአዲስ አበባ እንድታካፍል የተለያዩ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑ ታውቋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ በአራት ቀን ቆይታው ሁለቱ ከተሞች እህትማማች የሆኑበትን አሥረኛ ዓመት በዓል ከአዲስ አበባ አቻው ጋር እንደሚያከብር ታውቋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የሁለቱ ከተሞች ንግድ ምክር ቤቶች የቢዝነስ ፎረም ይካሄዳል፡፡ አቶ ወርቁ እንደገለጹት፣ የሁለቱ ከተሞች ግንኙነታቸውን ለማጠናከር የቢዝነስ ፎረሙ ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል፡፡

ከወራት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ድሪባ የሚመራ የልዑካን ቡድን ወደ ላይፕዚሽ ከተማ ተጉዞ ነበር፡፡ በወቅቱ የሁለቱን ከተሞች አሥረኛ ዓመት በዓል ከመከበሩም በላይ፣ የተለያዩ የኢንቨስትመንትና የንግድ ፎረሞች ተካሂደዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...