Friday, December 9, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ስፖርትቅዱስ ጊዮርጊስ በአልጄሪያ ደደቢት በሲሸልስ ቅዳሜ ይጫወታሉ

  ቅዱስ ጊዮርጊስ በአልጄሪያ ደደቢት በሲሸልስ ቅዳሜ ይጫወታሉ

  ቀን:

  በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮናና በአፍሪካ ክለቦች ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ላይ አገሪቱን የሚወክሉት ቅዱስ ጊዮርጊስና ደደቢት ከሜዳቸው ውጪ የሚያደርጉትን የመጀመርያ ጨዋታ ቅዳሜ ያከናውናሉ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ትናንት ምሽት ወደ አልጄሪያ አልጀርስ የተንቀሳቀሰ ሲሆን፣ ደደቢት ደግሞ ዛሬ ምሽት በኬንያ አየር መንገድ ወደ ሲሸልስ ያመራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
  የፕሪሚየር ሊጉ የአምናው አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ በአህጉራዊው የክለቦች ሻምፒዮና ላይ በተደጋጋሚ በመቅረብ ከአገሪቱ ክለቦች በቀዳሚነት ይጠቀሳል፡፡ በውጤት ደረጃም ቢሆን በክለቦች ሻምፒዮናም ሆነ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ከአገሪቱ ክለቦች የተሻለ ታሪክ በማስመዝገብ ቀዳሚ ነው፡፡
  ከተመሠረተ በመጪው ታኅሣሥ 80 ዓመት የሚደፍነው አንጋፋው ቅዱስ ጊዮርጊስ ዘንድሮ 17ኛ ዓመቱን ያስቆጠረው የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ 11 ጊዜ በማንሳትም ብቸኛ ያደርግዋል፡፡ በመጪው ቅዳሜ ከአልጄሪያው ኤምሲ ኤል ኦልማን ጋር በአልጀርስ የሚጫወተው ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ በአህጉራዊው መድረክ ጠንካራ ተፎካካሪ መሆን የሚያስችለውን ዝግጅት ማድረጉ እየተነገረ ባለበት በዚህ ወቅት አዲስ ከብራዚልና ከኡጋንዳ የመጡ ሁለት ፕሮፌሽናሎች ትናንት ምሽት ወደ አልጀርስ ካመራው ልኡክ ጋር መካተታቸው ታውቋል፡፡
  የቅዱስ ጊዮርጊስ ምክትል አሠልጣኝ ፋሲል ተካልኝ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ከቡድኑ ጋር አብረው ከሚጓዙት ፕሮፌሽናሎች ብራዚላዊው ተጨዋች ከዝውውር ጋር በተያያዘ ይህን ማብራያ እስከሰጠበት ጊዜ ድረስ ያልተጠናቀቀለት ጉዳይ መኖሩን ተናግረዋል፡፡ የተጋጣሚያቸውን ወቅታዊ አቋም በተመለከተ ምክትል አሠልጣኙ፣ ‹‹ኤምሲኤል ኦልማን በውድድር ዓመቱ በአገሪቱ የሊግ ውድድር ያደረጋቸው የጨዋታ እንቅስቃሴዎች ሙሉ የሚያሳዩ መረጃዎችን አግኝተናል፡፡ ለዚያ የሚመጥን ዝግጅትም አድርገናል፤›› ብለዋል፡፡ ጨዋታው ቅዳሜ 12 ሰዓት ላይ መሆኑን ጭምር ተናግረዋል፡፡
  የአምናው የክለቦች ጥሎ ማለፍ አሸናፊ የደደቢት እግር ኳስ ክለብ በተመሳሳይ ከሲሸልሱ ኮት ዴ ኦርን ጋር ቅዳሜ ለአፍሪካ ክለቦች ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይጫወታል፡፡ ቡድኑ ዛሬ ምሽት የኬንያን አየር መንገድ ተጠቅሞ በነገው ዕለት ሲሸልስ እንደሚደርስ ዋና አሠልጣኙ ኢንስትራክተር ዮሐንስ ሳሕሌ ተናግረዋል፡፡
  እንደ ክለቡ ዋና አሠልጣኝ፣ የደደቢት ተጋጣሚ ኮት ዴ ኦርን በአገሪቱ የሊግ ውድድር ጠንካራ ተብለው ከሚጠቀሱ ክለቦች አንዱ ሲሆን፣ ሐቻምና የሊጉ ሻምፒዮና በመሆኑ በአፍሪካ ክለቦች ሻምፒዮና ላይ ተሳታፊ እንደነበር ተናግረዋል፡፡ ከዚህ አኳያ ከቡድናቸው ተጨዋቾች በጉዳት ምክንያት ያሬድ ዝናቡ፣ ሔኖክ ካሳሁንና በረኛው ታሪኩ ጌትነት ከቡድኑ ጋር አብረው አይጓዙም፡፡ የተቀሩት ግን ለጨዋታው የሚያስፈልገውን ዝግጅት ማድረጋቸውን ነው አሠልጣኙ ያስረዱት፡፡
  ቅዱስ ጊዮርጊስም ሆነ ደደቢት ተጋጣሚዎቻቸውን በሜዳቸው በሚያደርጉት ጨዋታ በአሸናፊነት መውጣት ከቻሉ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከጋናው አሻንቲ ኮቶኮእና ከቱኒዚያው ሴፋክሲያ አሸናፊ ጋር በቀጣይ ሲጫወት ደደቢት በበኩሉ ከናይጄሪያና ቡርኪናፋሶ ክለቦች አሸናፊ ጋር እንደሚገናኝ ይጠበቃል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው ጭፍጨፋና ሥጋቱ

  ኦሮሚያ ክልል ከቀውስ አዙሪት መላቀቅ ያቃተው ይመስላል፡፡ ከ200 በላይ...

  እናት ባንክ ካፒታሉን ወደ አምስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ወሰነ

  መጠባበቂያን ሳይጨምር የባንኩ የተጣራ ትረፍ 182 ሚሊዮን ብር ሆኗል እናት...

  ቡና ባንክ ዓመታዊ ትርፉን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ማሻገር ቻለ

  ቡና ባንክ በ2014 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔውን ለመጀመርያ...