የደም ልገሳ በቫላንታይን ቀን
የፊታችን ቅዳሜ የሚከበረውን የቫላንታይን ቀን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የደም ልገሳ ፕሮግራም ተዘጋጀ፡፡ ‹‹በፍቅረኞቸ ቀን በፍቅር የምንለግሰው – ፀጋችን – ደማችን›› በሚል መሪ ቃል፣ በዋዜማው የካቲት 6 እና በዕለቱ የካቲት 7 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢትዮ ኩባ አደባባይ የሚካሄደውን የደም ልገሳ ፕሮግራም ያዘጋጀው፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከሻዶም ሚዲያ ኮሚዩኒኬሽን ጋር በመሆን ነው፡፡