በተለያዩ ውጭ አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዓምና (2009 ዓ.ም.) 4.6 ቢሊዮን ዶላር ወደ ኢትዮጵያ በመላክ ከፍተኛ የውጭ የምንዛሪ ምንጭ ሆነው እያገለገሉ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዳያስፖራና ቢዝነስ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አስታወቁ፡፡ ጥቅምት 30 ቀን 2010 ዓ.ም. በተካሄደው የመጀመሪያው የዳያስፖራ ጉዳዮች የጋራ መድረክ አጀንዳ ላይ ሚኒስትር ዴኤታው አክሊሉ ኃይለሚካኤል (ዶ/ር)፣ ይህ ገቢ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ለማስጨረስ ከተገመተው መጠን በላይ መሆነን ተናግረዋል፡፡