Saturday, June 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊቫላንታይንና እናትነት

ቫላንታይንና እናትነት

ቀን:

በዳንኤል ቡርሳ

በ270 ዓ.ም. አካባቢ የነበረው የሮማ ንጉሥ ካላውዲየስ ሁለተኛ አንድ አስደንጋጭ አዋጅ አወጀ፡፡ በሮም የሚኖር ማንኛውም ወንድ ወጣቶች ትዳር እንዳይዙና በውትድርና እንዲያገለግሉ ብቻ አስለፈፈ፡፡ ታዲያ በየዘመኑ የሚፈጠሩ ጀግኖች ደግሞ አይጠፋም እንደ ቄስ ቫላንታይን ያሉ፡፡ ቄስ ቫላንታይን በዘመኑ የሮም ቄስ ሆኖ የሚያገለግል የነበረ ሲሆን የንጉሡን አዋጅ ከቁብ ሳይቆጥር የሮም ወጣቶችን በድብቅ ያጋባ ጀመር፡፡ በኋላም ይህ ተግባሩ በሮም ነገሥታት ዘንድ ሲሰማ ትልቅ ቁጣና ብስጭት ፈጠረ፡፡ የሮም ነገሥታትም መከሩ ይህን ደፋር ምን እናድርገው? እንዴትስ እንቅጣው? ከቶስ ምን ብናደርገው ነው ለሮም ሕዝብና ለሌሎች እንደሱ ላሉ ደፋር ቄሶች ትምህርት የምንሰጠው ብለውም ተጨነቁ፡፡ በመጨረሻም ቄስ ቫላናታይን ለመቀጣጫ በስቅላት እንዲቀጣ ወሰኑ ቄስ ቫላናታይንም በወርሃ የካቲት በሰባተኛው ቀን ለፍቅር ሲል ሕይወቱን ሰጠ፡፡

በእርግጥ ስለቄስ ቫላንታይን የተለያዩ አወዛጋቢ ታሪኮች ቢኖሩም ይህኛው ግን ሚዛን የሚደፋውና ብዙ የታሪክ አዋቂዎች የሚስማሙበት ነው፡፡ ይህ ቀንም የፍቅር ቀን ተብሎ እንዴት መከበር እንደጀመረም ብዙ አከራካሪ ነገሮች ቢኖሩትም በዓለም ላይ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ፍቅረኛሞች በዕለቱ ፍቅራቸውን ለማደስና ለማጠናከር እንደ አበባና ካርድ የመሳሰሉትን ስጦታ በመለዋወጥ ስለሚያከሩትም ይመስላል ወርሃ የካቲት የፍቅር ወር፣ የካቲት ሰባትም የፍቅር ቀን ተብሎ የሚጠራው፡፡ በአገራችንም ይህ ቀን በተለይም በመዲናችን አዲስ አበባ በተለያዩ ፕሮግረሞች መከበር ከጀመረ ከራረመ፡፡

- Advertisement -

ቄስ ቫላንታይን ለፍቅር ሲል በተሰዋባት በዚች ቀን በአገራችን 35 የሚሆኑ እናቶች ሕይወት ለመስጠትና አዲስ ተስፋ ያለው ትውልድ ለመተካት በሚያደርጉት ጥረት ውድ ሕይወታቸውን ያጣሉ፡፡

ጥናቶች እንደሚያሳዩት እስከ 30 በመቶ የሚሆኑት እናቶች ሕይወታቸውን የሚያጡት ከፍተኛ ደም መፍሰስ ጋር ተያይዞ እንደሆነ ያሳያል፡፡ በዚች ዕለት ብቻ አስር እናቶች በአገራችን ደም በማጣት ይሞታሉ በእርግጥ በአሁኑ ጊዜ ወደ ጤና ተቋማት እየሔዱ የሚወልዱ እናቶች ቁጥር በመጨመሩ የእናቶች ሞት እየቀነሰ መምጣት መጀመሩ እሙን ነው፡፡

እናት ለቤተሰብ ለትዳር፣ ለማኅበረሰብ፣ ለአገር… በቃ እናት ለሁሉም ነገር መሰረት ናት፡፡ ስለእናት ለመጻፍ መሬት ወረቀት ውቅያኖሶች ቀለም ቢሆኑ ሁሉ በእርግጥም አይበቁም በአጠቃላይ እናት ፍቅር ናት ወሩ ደግሞ የፍቅር፡፡ በዚች የፍቅር ቀንና የፍቅር ወር ለእናቶቻችን የማያልቀውንና የስጦታዎች ሁሉ ስጦታ የሆነውን ከክቡር የሰው ልጅ ብቻ የሚገኘውን ስጦታ እንስጥ… የደም ልገሳ፡፡

እነቄስ ቫላንታይን ለፍቅር ሲሉ ነው ውድ ሕይወታቸውን የሰውት እኛ ግን ለፍቅር ስንል ይህን ይዘነው የምንዞረው የአምላክ ስጦታ በሆነው በደማችን ሕይወትን፣ ቤተሰብን፣ ማኅበረሰብን መታደግ ይቻላል፡፡

ከአዘጋጁ፡- ጽሑፉ የጸሐፊውን አመለካከት የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...