Tuesday, October 3, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበአገር አቀፍ ደረጃ የከርሰ ምድር ውኃ ካርታ ሊዘጋጅ ነው

በአገር አቀፍ ደረጃ የከርሰ ምድር ውኃ ካርታ ሊዘጋጅ ነው

ቀን:

የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር በአገር አቀፍ ደረጃ የከርሰ ምድር ውኃ ካርታ ለማዘጋጀት ማቀዱን ገለጸ፡፡

የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትር አቶ እያሱ አብርሃ (ዶ/ር) የስምንት ወራት የሥራ አፈጻጸማቸውን መጋቢት 12 ቀን 2009 ዓ.ም. ለፓርላማ ባቀረቡበት ወቅት እንደተናገሩት፣ የአፈር ለምነት ካርታ ዝግጅት ለግብርናው ዘርፍ እያስገኘ ካለው አስተዋጽኦ በመነሳት የከርሰ ምድር ውኃ ካርታ ለማዘጋጀት በሚኒስቴሩ ታቅዷል፡፡

አገሪቱ አሁን ባለችበት ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ዝናብን ብቻ ጠብቆ የግብርና ዘርፉን መምራት እንደማይቻል ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

አገሪቱ በተደጋጋሚ እየገጠማት የሚገኘውን የድርቅ አደጋ መቋቋም የምትችለው አማራጭ የውኃ ምንጭን መጠቀም ሲቻል መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም እያንዳንዱ አርሶ አደር ከዝናብ ውጪ የውኃ አማራጭ እንዲኖረው የተያዘውን ዕቅድ ለመደገፍ፣ በአገር አቀፍ ደረጃ የከርሰ ምድር ውኃ የሚገኝባቸውን አካባቢዎች ከእነ ውኃ መጠኑ የሚያሳይ ካርታ እንደሚዘጋጅ ጠቁመዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በሶማሌ፣ በኦሮሚያና በአንዳንድ የደቡብ ክልል አካባቢዎች በድርቅ መመታታቸው ይታወቃል፡፡ በተለይ በሶማሌና በኦሮሚያ ክልሎች ድርቁ በሰው ሕይወት ላይ አደጋ ያደርሳል የሚል ከፍተኛ ሥጋት አለ፡፡

ወቅታዊ ከሆነው ድርቅ ጋር በተያያዘ 5.6 ሚሊዮን ሕዝብ ዕለታዊ ዕርዳታ እንደሚያስፈልገው መንግሥት ይፋ ማድረጉ ይታወቃል፡፡ የተጠቀሱት ተረጂዎች የሚያስፈልጋቸውን ዕለታዊ ዕርዳታ እስከ መጪው የመኸር ወቅት ለማቅረብ 20 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልግም ተገልጿል፡፡

በወቅታዊው የዝናብ እጥረት ምክንያት ዕለታዊ የምግብ ዕርዳታና ድጋፍ ከሚያስፈልገው 5.6 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በተጨማሪ፣ ዘላቂ የዝናብ እጥረት በሚስተዋልባቸው አካባቢዎች 7.9 ሚሊዮን ተጨማሪ ኢትዮጵያውያን በልማታዊ ሴፍቲኔት ታቅፈው የገንዘብና የምግብ ድጋፍ በየዓመቱ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

መንግሥት በዚህ ፕሮግራም ለታቀፉ ተረጂዎች ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር በቢሊዮኖች ብር በየዓመቱ በማውጣት ላይ ይገኛል፡፡ ባለፉት ስምንት ወራት ውስጥም 6.6 ቢሊዮን ብር ወጪ መደረጉን የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...