Saturday, January 28, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር 25 ሚሊዮን ብር በጀት ተያዘ

ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር 25 ሚሊዮን ብር በጀት ተያዘ

ቀን:

በኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሥር ለሚገኘው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ምክር ቤት ለምርምር በጀት የሚውል 25 ሚሊዮን ብር መበጀቱን 46 የፕሮጀክት ሐሳቦች ተመርጠው ወደ ተግባር የሚለወጡበት ሁኔታ በመመቻቸት ላይ መሆኑን አቶ መሐሙዳ አህመድ ጋዕዝ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ አስታወቁ፡፡

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዴሚ በብሔራዊ ምርምር ካውንስል፣ አደረጃጀትና አሠራር ላይ ትኩረት አደርጐ የካቲት 5 ቀን 2007 ዓ.ም. ያካሄደውን አገር አቀፍ ጥናት አስመልክተው አቶ መሐሙዳ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ገንዘቡ የተገኘው ከመንግሥት ሲሆን፣ የተጠቀሱት የፕሮጀክት የተመረጡትም 200 ተመራማሪዎች እያንዳንዳቸው ካቀረቧቸው የፕሮጀክት ሐሳቦች መካከል ነው፡፡

ከአንድ መቶ በላይ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የተቋማት መሪዎች፣ ተመራማሪዎች፣ በምርምርና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ የተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ተወካዮች በተሳተፉበት በዚሁ አገር አቀፍ መድረክ ላይ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚከናወኑ የምርምር ሥራዎችን ለመምራትና ለማስተባበር የሚያስፈልገውን የብሔራዊ ምርምር ምክር ቤት አደረጃጀትና አሠራር አስመልክቶ በተለያዩ ርዕሶች ላይ ለአንድ ዓመት ተኩል ያህል ሲካሄዱ የቆዩ የጥናት ውጤቶች ቀርበዋል፡፡

ጥናቱን ካቀረቡት የቡድኑ አባላት መካከል ፕሮፌሰር ጽጌ ገብረማርያም የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዴሚ መሥራች፣ የቦርድ አባልና የጥናት ቡድኑ ሰብሳቢ ይገኙበታል፡፡ ፕሮፌሰሩ ጥናታቸውን አስመልክተው እንዳብራሩት፣ ብሔራዊ የምርምር ምክር ቤቱ አሁን ያለው በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሲሆን፣ ወደፊት ነፃና ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርና ተጠሪነቱ ለመንግሥት ሆኖ የሚቋቋምበት መንገድ እንደሚመቻች ተናግረዋል፡፡

ራሱን ችሎ በአገር ደረጃ የሚቋቋመውም ብሔራዊ የምርምር ምክር ቤት ከሳይንቲስቶችና ከምሁራን ጋር እየተመካከረ ቅድሚያ በሚሰጣቸውና አገር ሊለውጡና ሊያሳድጉ የሚችሉ አጀንዳዎችንና የምርምር ፕሮግራሞችን እንደሚያካሄድ ገልጸዋል፡፡

ምርምር የሚሠሩ ሰዎች የሚሠለጥኑበትን፣ የትምህርት ጥራት ምን መሆን እንዳለበት፣ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ ከመግባታቸው በፊት ገና ሁለተኛ ደረጃ እያሉ ሰብዓዊነት፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂን የመሳሳሉ ትምህርቶችን እንዴት ማግኘት እንዳለባቸው፣ ዩኒቨርሲቲም ከገቡ በኋላ ስለምርምር ያላቸው ግንዛቤ እንዴት ማደግ እንዳለበት፣ በድህረ ምረቃ፣ በዶክትሬት፣ የሚካሄደው ምርምር ለአገር ፋይዳው ምንድነው የሚሉትም መሠረተ ሐሳቦች በጥናቱ ተዳስሰዋል፡፡

ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዴሚ ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተር፣ አካዴሚው የሳይንስ ማዕከል ለማቋቋም በማካሄድ ላይ ያለው ጥናት 95 በመቶ ያህሉ እንዳለቀ አስረድተዋል፡፡ የዲዛይኑ ሥራም ተገባዷል፡፡ ማዕከሉንም ለማቋቋም የታቀደው በአካዴሚው ቅጥር ግቢ ሲሆን፣ ለሕንፃውም ግንባታ ከመንግሥትና ከተለያዩ ተቋማት ተገቢው ድጋፍ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቅዱስ ሲኖዶስ ሦስቱን ጳጳሳት ስልጣነ ክህነታቸውን አንስቶ አወገዘ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ሰሞኑን ጥር 14...

አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ ከህብረት ባንክ ቦርድ አባልነት ለቀቁ

አንጋፋው የፋይናንስ ባለሙያ አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ ከህብረት ባንክ ቦርድ...

አቶ በረከት ስምኦን ከእስር ተፈቱ

ከአራት ዓመታት በፊት በተከሰሱበት በከባድሙስና ወንጀል ስድስት ዓመታት ተፈርዶባቸው...

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ ቢሯቸው እንደገቡ የፖለቲካ አማካሪያቸው ስለ ሰሜኑ ግጭት የሰላም ስምምነት አተገባበር ማብራሪያ ለመጠየቅ ገባ]

ክቡር ሚኒስትር ጥሰውታል? እንዴ? እስኪ ተረጋጋ ምንድነው? መጀመርያ ሰላምታ አይቀድምም? ይቅርታ...