Monday, September 25, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየሴቶች የአምስት ኪሎ ሜትር ሩጫ ሊካሄድ ነው

የሴቶች የአምስት ኪሎ ሜትር ሩጫ ሊካሄድ ነው

ቀን:

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ከዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ጋር በማያያዝ ‹‹ቅድሚያ ለሴቶች›› በሚል ስያሜ የሴቶች ሩጫ ሲያዘጋጅ ቆይቷል፡፡ በኢትዮጵያ የሴቶችን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ስኬት በመዘከር፣ ኢትዮጵያውያት በማኅበረሰቡ ውስጥ ያላቸውን ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ለማስገንዘብ፣ ከፍ ለማድረግና ለበለጠ ስኬት ሴቶችን የሚመለከቱና የሚዘክሩ መልክዕቶች ባካሄዳቸው የሩጫ ውድድሮች አስተላልፏል፡፡
የዘንድሮው ሩጫ ‹‹አገርን ለማልማት ሴቶችን እናሳትፍ›› በሚል መርሕ ከ10,000 በላይ ሴቶች የሚሳተፉበት የአምስት ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር እሑድ መጋቢት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ማድረግ የሚያስችል ዝግጅት ማጠናቀቁን ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከትላንት በስቲያ በካፒታል ሆቴል አስታውቋል፡፡
ሰኞ የካቲት 9 ቀን 2007 ዓ.ም. በእናት ባንክ ሁሉም ቅርንጫፎች ምዝገባው የሚጀምር መሆኑንና ለግል ተመዝጋቢዎችና በድርጅት ለሚመዘገቡ ደግሞ በታላቁ ሩጫ ቢሮ መሆኑን የውድድሩ አዘጋጆች ገልጸዋል፡፡
ውድድሩ በተለያዩ የኑሮ ደረጃና ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሴቶች በአንድነት የሚሳተፉበት እንደሆነ፣ ይህም ሴቶችን እርስ በርስ የልምድና የሕይወት ተሞክሮ እንዲለዋወጡ ለማድረግ ዓይነተኛ መንገድ መሆኑም አስታውቋል፡፡ ዘንድሮ በውድድሩ ከአንድ እስከ አሥር ለሚወጡ አሸናፊ አትሌቶች በድምሩ ከ80,000 ብር በላይ የገንዘብ ሽልማት መዘጋጀቱም ታውቋል፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የቤት ባለንብረቶች የሚከፍሉትን ዓመታዊ የንብረት ታክስ የሚተምን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

በአዋጁ መሥፈርት መሠረት የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የንብረት ታክስ መጠን...

እንደ ንብረት ታክስ ያሉ ወጪን የሚያስከትሉ አዋጆች ከማኅበረሰብ ጋር ምክክርን ይሻሉ!

የመንግሥትን ገቢ በማሳደግ ረገድ አስተዋጽኦ እንዳላቸው የሚታመኑት የተጨማሪ እሴት...

ለዓለምም ለኢትዮጵያም ሰላም እንታገል

በበቀለ ሹሜ ያለፉት ሁለት የዓለም ጦርነቶች በአያሌው የኃያል ነን ባይ...