Thursday, November 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየጀግኖች አርበኞች ማኅበር የግራዚያኒ ሐውልት እንዲፈርስ ዳግመኛ ጥሪ አቀረበ

የጀግኖች አርበኞች ማኅበር የግራዚያኒ ሐውልት እንዲፈርስ ዳግመኛ ጥሪ አቀረበ

ቀን:

ፋሺስት ኢጣሊያ ከ78 ዓመት በፊት በአዲስ አበባ ባደረሰው ጅምላ ጭፍጨፋ ዋና ተዋናይ ለነበረው ማርሻል ሮዶልፍ ግራዚያኒ ከሮም ወጣ ባለች ኤሬል መንደር የተሠራለት ሐውልት እንዲፈርስ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ዳግመኛ ጥሪ አቀረበ፡፡

የካቲት 12 ቀን 2007 ዓ.ም. የሚታሰበውን የኢትዮጵያውያን ሰማዕታት ዕለት አስመልክቶ የጀግኖች አርበኞች ማኅበር፣ ‹‹በፋሺስት ጣሊያን የተጨፈጨፉት ኢትዮጵያውያን ሰማዕታት ለዘላለም ሕያው ናቸው›› በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ፣ በአዲስ አበባ የፋሽስቱ መሪ የቤኒቶ ሙሶሎኒ ወኪልና ተጠሪ የነበረው ማርሻል ሮዶልፎ ግራዚያኒ በሦስት ተከታታይ ቀናት በግፍ የተገደሉት ከ30,000 በላይ ሰማዕታት ተጠያቂ ነው ብሏል፡፡

ሁለቱ ኢትዮጵያውያን አርበኞች አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም በገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት በግራዚያኒ ላይ በጣሉት የቦምብ አደጋ ተከትሎ በተለያዩ አካባቢዎች ፋሺስቶች ላደረሱት ፍጅት የተሰዉት ሰማዕታት ሕያው ናቸው ያለው ማኅበሩ፣ ከሁለት ዓመት በፊት የተሠራው የግራዚያኒ ሐውልት በወቅቱ እንዲፈርስ መጠየቁ ይታወሳል፡፡

ከኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ሌላ ጣሊያናውያን ባሳዩት ተቃውሞ ሐውልቱ እንዲሸፈን መደረጉ በአዎንታዊ መልኩ የተመለከተው ማኅበሩ የግራዚያኒ ሐውልት ሙሉ ሙሉ መፍረስ አለበት ብሏል፡፡

ሐሙስ ዕለት ስድስት ኪሎ በሚገኘው የካቲት 12 ቀን ሰማዕታት ሐውልት ታስቦ የሚውለው የሰማዕታት ቀን፣ በኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት ዘመን ብሔራዊ በዓል ሆኖ መሥሪያ ቤቶች ተዘግተው ይከበር የነበረ ቢሆንም፣ ደርግ ሥልጣን ላይ ከወጣበት ከ1967 ዓ.ም. ጀምሮ ብሔራዊ በዓልነቱ መሠረዙ ይታወሳል፡፡

በተያያዘ ዜና ከ11 ቀናት በኋላ የሚከበረውን የዓድዋ ድል 119ኛ ዓመት በደማቅ ሥነ ሥርዓት ለማክበር መዘጋጀቱን፣ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

‹‹የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓልን የካቲት 23 ቀን ስናከብር በዳግማዊ አፄ ምኒልክ አመራር የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የሕይወት መስዋዕትነት ከፍለው በርካታ ቁጥር ያላቸው ወገኖቻችን አካላቸው ጎድሎ የአገራችንን ነፃነት ላስከበሩት ያለንን ከበሬታ እንገልጻለን፤›› ብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...