Saturday, April 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየውኃ እጥረት የአዲስ አበባን አረንጓዴ የልማት ሥራዎች እያደናቀፈ ነው ተባለ

የውኃ እጥረት የአዲስ አበባን አረንጓዴ የልማት ሥራዎች እያደናቀፈ ነው ተባለ

ቀን:

በሺቢያምፅ ደምሰው

በአዲስ አበባ ውበትና አረንጓዴ ልማት ሥራዎች ላይ የውኃ እጥረት ተፅዕኖ እየፈጠረ እንዲሁም የደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት ያለመዳበር፣ የሕዝብ መፀዳጃ ቤቶች እጥረት፣ ሕገወጥ የእንስሳት ዝውውርና ንግድም የከተማዋን ፅዳትና ውበት እየተፈታተኑ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ ጽሕፈት ቤት ከውበት መናፈሻና ዘላቂ ማረፊያ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር የካቲት 6 ቀን 2007 ዓ.ም. ባዘጋጀው መድረክ፣ የውኃ እጥረት በአረንጓዴ ልማቱ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እየፈጠረ፣ የሚተከሉት ችግኞች እንዲሁም የሣር መሬቶች ከጥቅም ውጪ እየሆኑ እንደሚገኙም አስታውቀዋል፡፡

ከተማዋ በፅዳት በኩል በርካታ ለውጦችንና መሻሻልን ማምጣቷን አንዳንድ የከተማዋ የፅዳት ውበትና አረንጓዴ ልማት ተሳታፊዎች አውስተው፣ በሚፈለገው ደረጃ እንዳይሠሩ አንዳንድ ልማታዊ ሥራዎች መጓተት፣ የጐዳና ተዳዳሪዎች መበራከት፣ ሕገወጥ የጐዳና ላይ ንግድ መጨመርና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች እያደናቀፏቸው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ሥራ አስኪያጅ አቶ ኃይሌ ፍሥሐ፣ ከፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ጋር በተያያዘ በከተማዋ በርካታ መሻሻሎች ባለፉት ጥቂት ዓመታት መምጣቱን፣ ያሉትንም ችግሮች ለማስወገድ የፍሳሽና ደረቅ መጓጓዣ መኪናዎችን አስተዳደሩ እንደገዛ ተናግረዋል፡፡

የቆሻሻ ማስተላለፊያ ትቦዎችን ካለፈው ዓመት በተሻለ መልኩ ለመዘርጋት መታሰቡን፣ ከመፀዳጃ ቤት እጥረት ጋር በተያያዘ የከተማው አስተዳደር ባለፈው ዓመት 810 የሚሆኑ ቋሚና ተንቀሳቃሽ መፀዳጃ ቤቶች መገንባቱን፣ በአሁኑ ዓመትም በርካታ መፀዳጃ ቤቶችን ገንብቶ ሥራ ላይ ለማዋል ወደ ሥራ መገባቱን ገልጸዋል፡፡

ከእንስሳት ዝውውሩና ንግዱ ጋር በተያያዘ በከተማዋ ችግሩ መኖሩን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ የገለጹ ሲሆን፣ ይህንንም ችግር ለመቅረፍ ቋሚ የመሸጫ ቦታዎች እንደሚመቻቹ እንዲሁም ቋሚ የቄራ መንደር ለመገንባትም ጥናቶች እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አቶ ኃይሌ የውኃ እጥረት በከተማዋ እንዳለ አምነው፣ የከተማው አስተዳደርም ችግሩን ለማቃለል ባለፉት ወራት ወደ 100,000 ሜትር ኪዩብ ውኃ ወደ ሥርጭት ማስገባታቸውን፣ ያም ሆኖ ግን የከተማዋን የውኃ ችግር መቅረፍ እንዳልቻሉ፣ በቀጣይ ጥቂት ወራትም በሁሉም የመዲናይቱ አቅጣጫዎች የውኃ እጥረቱን ለመቅረፍ የተለያዩ ሥራዎች እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡

ከንቲባ ድሪባ፣ ከተማዋ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ጀምሮ በፅዳት፣ ውበትና አረንጓዴ ልማቱ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣቷን ጠቁመው፣ ይህም ሆኖ ግን የአፍሪካ መዲና፣ ለበርካታ አኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ዝግጅቶች ተመራጭ እንደመሆኗ ‹‹ለአዲስ አበባ የሚመጥን ሥራ አልተሠራም፤ መሥራት አለብን፤›› ብለዋል፡፡

አስተዳደሩ ባለፈው ዓመት 5,000 የሚሆኑ የጐዳና ተዳዳሪዎችን በተለያዩ የሙያ ዘርፎች አሠልጥኖ ወደ ሥራ እንዳስገባ ከንቲባው ገልጸው፣ በዘንድሮው ዓመትም 10,000 ለሚሆኑ የጐዳና ተዳዳሪዎች የሙያ ሥልጠና ለመስጠት፣ ለግማሾቹ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የቀሩትንም ሥልጠናቸውን እንደጨረሱ ወደየመጡበት አካባቢ ለመመለስና በሥራ የሚሰማሩበትን መንገድ ለማመቻቸት መታሰቡን ተናግረዋል፡፡ ከታዳጊ ከተሞችና ከሀገሪቱ ገጠራማ አካባቢዎች ወደ መዲናይቱ የሚደረገውን ፍልሰት ለመቀነስ የከተማ አስተዳደሩ ከክልሎችና ከየከተማ አስተዳደሮች ጋር በጋራ ለመሥራት ዝግጅቱን ማጠናቀቁንም አክለዋል፡፡

አስተዳደሩ በ2007 ዓ.ም. የከተማዋን ውበትና የአረንጓዴ ልማት ለማሳደግ ለተለያዩ ዝግና ክፍት ፓርኮች ግንባታ ከ254 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት መድቦ በመሥራት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ለዘመናዊ የፅዳት ማሽነሪዎችና ማጓጓዣ ኮምፓክተር ተሽከርካሪዎች 280 ሚሊዮን ብር በሚደርስ ወጪ ተገዝቶ በሥራ ላይ እንደሚገኝም ሥራ አስኪያጁ ገልጸዋል፡፡

በ2006 ዓ.ም. የመንገድ ዳርቻዎችንና አካፋዮችን፣ አደባባዮችን፣ አረንጓዴ ቦታዎችን፣ ክፍትና ዝግ ፓርኮችን፣ የኮንዶሚንየም ሳይቶችንና ሌሎች በርካታ የልማት ሥራዎችን የሠሩ ባለሀብቶች፣ ግለሰቦች፣ ማኅበራት፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ባለሙት የካሬ ሜትር ስፋት፣ ባወጡት የገንዘብ መጠን፣ በፈጠሩት የሥራ ዕድል መጠን የሜዳልያና የዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡      

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተወግዘው የነበሩ ሦስቱ ሊቀጳጳሳትና 20 ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ውግዘት ተነሳ

_ቀሪዎቹ ሦስት ህገወጥ ተሿሚዎች የመጨረሻ እድል ተሰጥቷቸዋል ​ ጥር 14...

በሕወሓት አመራሮች ላይ ተመስርቶና በሂደት ላይ የነበረው የወንጀል ክስ ተቋረጠ

በቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤ,(ዶ/ር)ና ባለፈው ሳምንት በተሾሙት...

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...