Friday, December 2, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊሚድሮክ ኢትዮጵያ የላቀ አስተዋጽዖ ላበረከቱ ሠራተኞች ሽልማት ሰጠ

  ሚድሮክ ኢትዮጵያ የላቀ አስተዋጽዖ ላበረከቱ ሠራተኞች ሽልማት ሰጠ

  ቀን:

  ዘንድሮ ለ12 ጊዜ በመቻሬ ሜዳ በተዘጋጀው የሚድሮክ ሠራተኞች ቀን በሥራቸው ምስጉን የሆኑ ከ20ዎቹ ኩባንያዎች የተውጣጡ 74 ሠራተኞች የገንዘብና የሠርተፍኬት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

  በኮከብ ሠራተኛ፣ በኮከብ ሥራ አስኪያጅ፣ በዓመቱ ምርጥ የሠራተኛ ማኅበራት፣ በዓመቱ ምርጥ ማኔጅመንት፣ ዘርፍ የላቀ ድርሻ ላበረከቱ ሠራተኞች እንዲሁም ኩባንያዎች ሽልማት የሰጠ ሲሆን፣ ሌሎችም አጋር ኩባንያዎች የሽልማቱ ተቋዳሽ ሆነዋል፡፡

  ትረስት የጥበቃ እና የሰው ኃይል አገልግሎት፣ ደይ ላይት አፕላይድ ቴክኖሎጂ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በካምፓኒ ዘርፍ፤ በኮከብ ሥራ አስኪያጅነት የተመረጡት የሁዳ ሪል ስቴት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ቴዎድሮስ ሸዋረጋ ሲሆኑ፣ ሌሎችም ኮከብ የድርጅቱ ሠራተኞች ተሸልመዋል፡፡ በተጨማሪም አሊያንስ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ኩባንያና የመቻሬ ሜዳ ካፍቴሪያ ሠራተኞች በቡድን ተሸልመዋል፡፡

  የዓመቱ ምርጥ ሠራተኛ ተብለው ከተሸለሙት አቶ አምበሴ አሥራት በኤልፎራ አግሮ ኢንዱስትሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር መሥራት ከጀመሩ ስምንት ዓመታት አስቆጥረዋል፡፡ ለስድስት ዓመታት ያህል በዳይሬክተርነት የሠሩ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በማኔጂንግ ዳይሬክተርነት በማገልገል ላይ ይገኛሉ፡፡ ለሽልማቱ ካበቋቸው ነገሮች መካከል ግልጽ የአሠራር ሥርዓት መኖርና መልካም የሥራ ግንኙነት እንደሆኑ ይገልጻሉ፡፡ የሠራተኞች የእርስ በርስ መስተጋብርና ከአለቃቸው ጋር ያላቸው ጥሩ ግንኙነት ለሥራው ውጤታማነት ትልቁን ድርሻ ያበረክታል፡፡ ኩባንያው ለሠራተኞች ነፃ የትምህርት ዕድል፣ ነፃ ሕክምና እንዲኖር ማድረጉና ሌሎችም ሠራተኛውን ያበረታታል›› ይላሉ፡፡

  በዚህ መሠረትም ውጤት በማስመዝገባቸው ሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ በኩባንያዎቹ ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሠራተኞች በመቻሬ ሜዳ ኮርፖሬት ሴንተር ግቢ የካቲት 7 ቀን ባዘጋጀው የሽልማት ሥነ ሥርዓት አቶ አምበሴ ተካተዋል፡፡ ባስገኙት የሥራ ውጤትም የገንዘብና የሠርተፊኬት ሽልማት አግኝተዋል፡፡

  እንደ እሳቸው ገለጻ የተበረከተላቸው የገንዘብና የሠርተፊኬት ሽልማት በይበልጥ እንዲሠሩ ያነሳሳቸዋል፡፡ ‹‹የበለጠ ኃላፊነት ጭኖብኛል፡፡ ምርታማነትን በማሳደግ የድርጅቱን ትርፋማነት አረጋግጣለሁ፤›› ብለዋል፡፡ 

  በበዓሉ መክፈቻ ወቅት የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ኦፊሰር ዶ/ር አረጋ ይርዳው ዓመቱን ሙሉ ሲተጉ የከረሙ ሠራተኞችና ቤተሰቦች በአንድነት ተሰባስበው የጋራ በዓላቸውን ማክበራቸው የእርስ በርስ መደጋገፍ ውጤቱ ከፍተኛ እንደሆነ መገንዘብ የሚቻልበት መድረክ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የኩባንያዎቹ ቁጥር 21 መድረሱንና ይህም የሠራተኛ ቁጥር በማበራከትና አምራች ዜጋ ለመገንባት ለሚደረገው ርብርብ ቴክኖሎጂ ግሩፑ ያበረከተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

  እንደ እሳቸው ገለጻ በ2006 ዓ.ም. የኩባንያዎች ቁጥር 20 የነበረ ሲሆን፣ 21ኛው ኩባንያ ከሚድሮክ ጐልድ ሥር በማውጣት የማዕድን ኤክስፓሎሬሽን ኩባንያ ጨምሯል፡፡ ይኸውም ቀደም ሲል 6,022 የነበረውን የሠራተኞች ቁጥር ወደ 6,615 ከፍ ሊያደርገው እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

  ‹‹ሠራተኛ ደመወዝ ስለተጨመረ ብቻ አይበረታታም፡፡ ክብሩን መጠበቅና በመልካም ግንኙነት ሊያቀርቡት ግድ ይላል፤›› ያሉት ዶር አረጋ፣ አመቺ የሥራ ድባብ በመፍጠር የድርጅቱን ዓላማ ለማሳካት እንደሚተጉ ገልጸዋል፡፡

  በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ካሣሁን ፎሎ፣ ሚድሮክ ያዘጋጀው ፕሮግራም በሌሎችም ኩባንያዎች መዘውተር እንዳለበት ተናግረዋል፡፡ ‹‹አመርቂ የሥራ ውጤት ለማስመዝገብ አሠሪና ሠራተኛ የሚኖራቸው መልካም ግንኙነት ወሳኝ ነው፡፡ በዚህ መልኩ የተገኘ የሥራ ውጤት አስደሳች ይሆናል፡፡ የአገራችንን የቴክኖሎጂ ዕድገት ማረጋገጥ የሚቻለውም በዚህ ነው ውድድራችን በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከአገር ውጭም መሆን አለበት፡፡ ለዚህ ደግሞ ሠራተኞችን በማበረታታት የሚገኝ የሥራ ውጤት ትልቁን ድርሻ ይይዛል›› ብለዋል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...