ባለፈው ሳምንት መገባደጃ የሕትመት ብርሃን ያየው መጽሐፍ ‹‹የሕዳሴ አብዮት›› ነው፡፡ በአምስት የተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች በአምስት ጸሐፍት የቀረበው መድበል ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት፣ የኢትዮጵያ አብዮት፣ ሕዳሴውን እንደ ቬልቬት፣ ሰላማዊ ትግል እና የሕዳሴው አብዮት የሚሉ ርእሶችን ይዟል፡፡
በመድበሉ እንደተመለከተው፣ የ‹‹ሕዳሴ አብዮት›› በሚል ስያሜ በታተመው መጽሐፍ ውስጥ የተካተተው ተተግባሪ ሐሳብ መጪውን ጊዜ ካለፈው ዘመን ጉድፍ ለማንጻት በተለይ በባህል፣ በአመለካከትና በታሪክ የተገፉ ስብስቦች በዴሞክራሲያዊ ጥላ ስር በእኩል ውክልና ወደ አደባባዩ የሚወጡበት መንገድ በመፍትሔነት አስቀምጧል፡፡
በመድበሉ ሥራዎቻቸው የተካተተላቸው ጸሐፍት ሙሉነህ አያሌው፣ ኃይለ መስቀል በሸዋምየለህ፣ ዳዊት ታደሰ፣ እስክንድር ነጋ እና ተመስገን ደሳለኝ ናቸው፡፡