Tuesday, November 29, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ኪንና ባህልወሮታና ሽኝት በአየር መንገድ

  ወሮታና ሽኝት በአየር መንገድ

  ቀን:

  አቶ ታዬ አስፋው በኢትዮጵያ አየር መንገድ መዝገብ ቤት ለ39 ዓመታት ሠርተው ከሦስት ወር በፊት ጡረታ ወጥተዋል፡፡ ለሦስት ወራት ወደ ድርጅቱ ባይመጡም፣ ቅዳሜ የካቲት 7 ቀን 2007 ዓ.ም. ሙሉ ልብስ አድርገው ተገኝተዋል፡፡ ስናነጋግራቸው የዕድሜያቸውን እኩሌታ ያሳለፉበትን ድርጅት እንደዋዛ ጥለው ባለመውጣታቸው በደስታ ተሞልተው ነበር፡፡

  ዕለቱ ከአየር መንገዱ ጡረታ የወጡ ሠራተኞች እንዲሁም ድርጅቱን ከ25 ዓመት በላይ ያገለገሉ ሠራተኞች ሽልማት ያገኙበት ነበር፡፡ በጡረታ ከተሰናበቱ 71 ሠራተኞች አንዱ አቶ ታዬ፣ ‹‹ካደግኩበት፣ ልጅ ወልጄ ከሳምኩበት ድርጅት በክብር መሸኘት የሚያኮራ ነው፤›› ብለዋል፡፡

  ለረዥም ዓመት አገልግሎታቸው ዕውቅና ማግኘት ለሳቸውም ለተቀሩት ጡረተኞችም ተገቢ እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡ ጡረተኞችን አመስግኖ ከመሸኘት ጐን ለጐን አሁንም በሥራ ላይ የሆኑትን መሸለም ‹‹በድርጅቱና ሠራተኞቹ መካከል የቤተሰባዊነት ስሜት የሚፈጥር ነው፤›› ይላሉ፡፡

  የኢትዮጵያ አየር መንገድ መሰል ዝግጅቶች በየዓመቱ የሚያሰናዳ ሲሆን፣ በዕለቱ በድርጅቱ የሠራተኞች ክበብ አዳራሽ የተገኙ 211 ሠራተኞችና ጡረተኞች እያንዳንዳቸው ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡ 

  ከነዚህም መካከል 40 ዓመት ያገለገሉ አምስትና 35 ዓመት የሠሩ 37 ሠራተኞች (አንድ ከሮምና አንድ ከካይሮ የመጡ ሠራተኞችን ጨምሮ) ይገኙበታል፡፡ የተቀሩት 30 ዓመት ያገለገሉ 68 ሠራተኞች እና 25 ዓመት የሠሩ 30 ሠራተኞች (አራት ሠራተኞች ከሎሜ፣ አንድ ከሮም፣ ከቦምቤና ከኪሊማንጃሮ የመጡ) ናቸው፡፡

  የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም እንደተናገሩት፣ ድርጅቱ አሁን ለደረሰበት ስኬት የጀርባ አጥንት የሆኑት ሠራተኞቹ መመስገን አለባቸው፡፡ ለዓመታት ቀን ከሌት ተግተው መሥራታቸው አየር መንገዱ በአፍሪካ ትልቁ መሆን ከቻለበት ምክንያቶች ተጠቃሽ ነው ብለዋል፡፡

  በድርጅቱ በታማኝነትና በብቃት ያገለገሉና እያገለገሉ ያሉ ሠራተኞች አየር መንገዱ ለወጠናቸው ትልልቅ ህልሞች መሳካት ከፍተኛ ድርሻ አላቸው ብለዋል፡፡ አየር መንገዱ መዳረሻዎቹን በማስፋትና አየር መንገዱን በማሳደግ ረገድ እየሠራ ባለው ድርጅት ለዓመታት ከሠሩት ሠራተኞች አዳዲሶቹ ብዙ የሚማሩት እንዳለ አክለዋል፡፡

  ለ30 ዓመት በድርጅቱ የሠሩት አቶ ኃይለሚካኤል ደምሴ በበኩላቸው፣ በየዓመቱ የሚከበረው የሠራተኞች ቀን አየር መንገዱን ለማገልገል የገቡትን ቃል የሚያድሱበት እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ እሳቸውና ሌሎችም ለአየር መንገዱ ዕድገት አስተዋጽኦ ያደረጉ ሠራተኞች በሥራቸው የበለጠ እንዲተጉ የሚያደርግና ሠራተኞችን ለአንድ ዓላማ የሚያዋሕዳቸው እንደሆነ እምነታቸው ነው፡፡

  ተመሳሳይ ሐሳብ የሰጡን ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ኃይሉ የትኬት ቢሮዎች ኃላፊ ሆነው ለ25 ዓመታትያገለገሉ ሲሆን፣ ዕለቱ ሠራተኞች ቦታ እንደሚሰጣቸውና በድርጅታቸው እንደሚመሰገኑ የተንፀባረቀበት ነው ብለዋል፡፡ ለድርጅቱ ስኬት ምክንያት መሆናቸውን ከማስረገጥ ባሻገር የሠሩት ጥሩ የሥራ ድባብ እንዳለ እንዲገነዘቡ የሚያደርግ መሆኑን ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በችግር የተተበተበው የሲሚንቶ አቅርቦት

  ሲሚንቶን እንደ ግብዓት ተጠቅሞ ቤት ማደስ፣ መገንባት፣ የመቃብር ሐውልት...

  ‹‹የናይል ዓባይ መንፈስ›› በሜልቦርን

  አውስትራሊያ ስሟ ሲነሳ ቀድሞ የሚመጣው በተለይ በቀደመው ዘመን የባህር...

  ‹‹ልብሴን ለእህቴ››

  ለሰው ልጅ መኖር መሠረታዊ ፍላጎት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ ልብስ...

  የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የምርመራ ውጤት እስከምን?

  በፍቅር አበበ የትምህርት ጥራትን፣ ውጤታማነትንና ሥነ ምግባርን ማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ...