የሚያስፈልግዎ
በደቃቁ የተከተፈ ሽንኩርት
በደቃቁ የተከተፈ ቃርያ
ጨው
ዘይት
የጥብስ ቅጠል
ቁንዶ በርበሬ
ዱቄት
አዘገጃጀት
- ቴስቲ ሶያውን በፈላ ውኃ ውስጥ ከ2 ደቂቃ ላልበለጠ ጊዜ መቀቀል
- የተቀቀለበትን ውኃ በማጥለያ በደንብ ማጥለል
- በጋለ መጥበሻ ላይ ዘይቱ ሲፈላ የተቀቀለውን እና በደቃቁ የተከተፈውን ቴስቲ ሶያ ሽንኩርት፣ ቃርያ ጨው እንዲሁም ቁንዶ በርበሬና የጥብስ ቅጠል በመጨመር ቡናማ ቀለም እስከሚይዝ በደንብ መጥበስ
- የሳንቡሳውን ቂጣ በማዘጋጀት ከላይ አብስለንና ቀምመን ያዘጋጀነውን ቴስቲ ሶያ ለሳንቡሳው በተዘጋጀው ቂጣ ውስጥ በመጨመር በጋለ መጥበሻ ላይ ዘይቱ በደንብ ሲፈላ መጨመርና መጥበስ
- የቴስቲ ሶያ የምግብ አዘገጃጀት