Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ሥነ ፍጥረትላምፕሬይ - እባብ መሳዩ ዓሣ

ላምፕሬይ – እባብ መሳዩ ዓሣ

ቀን:

ላምፕሬይ ጨዋማና ጨዋማ ባልሆነ የውኃ ክፍል ሲኖሩ፤ በዙሪያው መምጠጫ አካሎች ያሉት ክብ አፍ፣ ሁለት ዓይኖችና አንድ አፍንጫ አላቸው፡፡ የትከሻና የዳሌ ላይ ክንፈ ዓሣ ባይኖራቸውም የጀርባ፣ የቂጥና የጭራ ላይ ክንፈ ዓሣ አላቸው፡፡ ደም መጣጭም ናቸው፡፡ ለሰው በምግብነት የሚያገለግሉት አጥንታም ዓሣዎች ላይ ጥገኛ ሆነው ደም በመምጠጥ ጉዳት ያደርሳሉ፡፡

እባብ መሳይ አካል አላቸው፡፡ አብዛኞቹ ዓሣ ላይ ከሚታየው ቅርፍ የፀዳ ነው፡፡ ተሙለጭላጭ ፈሣሽ የሚያወጣ የቆዳ ዕጢ ስላላቸው እነሱን በእጅ ለመያዝ በጣም አስቸጋሪ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ከአጥንት (ግንጭል) ይልቅ አፋቸው የተከበበው በልም አጽም ነው፡፡ በዚህም ምክንያት አፋቸው እንደተከፈተ ይዋኛሉ፡፡ ሆኖም ግን ይህ አፋቸው ብቃት ያለው መጣጭና አጣባቂ ክፍል ያለው ሲሆን፣ በሱም እራሳቸውን ከድንጋይና ከሌላ ዓሣ ጋር ማጣበቅ ያስችላቸዋል፡፡ ብዙውን ጊዜ ለመራባት ወደ ጨው አልባ የውኃ ክፍል ሲመጡ ፈጣን ወራጅ ውኃ ስለሚገጥማቸው አፋቸው ላይ ያለውን መጣበቂያ የአካል ክፍል ከድንጋይና ከሌላም ነገር ጋር በማያያዝ በውኃው ከመወሰድ ይድኑበታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ድንጋይ ላይ ለመጣበቅ ያላቸው ችሎታ ከፏፏቴ በላይ እንዲወጡ ይረዳቸዋል፡፡ በዚህም ጊዜ ከውኃ አካል ውጪ ሆነው የሚታዩበት አጋጣሚ አለ፡፡ ይህንንም በመመልከት ላምፕሬይ ዳገት የሚወጣ ዓሣ ተብሎ ይታወቃል፡፡ ወደ ወንዝ ዕንቁላላቸውን ሊጥሉ ሲሄዱ በተቻለ መጠን የውኃው መጠን ዝቅተኛ የሆነ ቦታ ይፈልጋሉ፡፡ እባብ መሳዮቹ ዓሣዎች የውኃ ፍጥነት ለመከላከል ድንጋይ ሰብስበው እንደ ግድብ የሚያገለግላቸውን የድንጋይ ጐጆ ይሠራሉ፡፡ ይህንን ድንጋይ የሚሰበስቡትም በአፋቸው ነው፡፡ ስለሆነም ላምፕሬይ ተባሉ፡፡ የግሪክ ትርጓሜውም ድንጋይ የሚልሱ እንደ ማለት ነው፡፡

አንዳንዶቹ ላምፕሬይ ምግባቸውን የሚያገኙት ራሳቸውን በማጣበቂያ መሳይ የአካል ክፍላቸው ከትልልቅ ዓሣዎች ጋር በማጣበቅ ሲሆን፤ ይህ አካላቸውም እንደመምጠጫ ያገለግላቸዋል፡፡ ጥርስ መሰል አካል ያለው ምላሳቸውም ከተጠቂው የዓሣ አካል ላይ ቀዳዳ ለመፍጠር ሲያገለግል በዚያም ውስጥ ደምና የአካል ፈሳሽ ይመጠጣል፡፡ ይህም ደም መጣጭ ያስብላቸዋል፡፡

  •  ማንይንገረው ሸንቁጥ ‹‹ባለአከርካሪዎች›› (2004 ዓ.ም.)

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...