Wednesday, March 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልምን የት?

ምን የት?

ቀን:

‹‹ምን ልሥራ? እንዴትስ?››

‹‹በርካታ ሰዎች ከምርጥና ድንቅ ሐሳቦቻቸው ጋር በድህነት ሲኖሩ፣ ጥቂቶች ደግሞ ብዙም ከማያስገርሙ ሐሳቦች ጋር ባለ ሀብት የሚሆኑት ለምን ይመስልሃል? ልዩነቱ ሥራን ቢዝነስ መሥርቶና በውስጡም ትክክለኛ ሲስተም ዘርግቶ በመሥራትና ባለመሥራት የሚመጣ ነው፡፡››

በጀርባው ሽፋን ላይ ይህን ቃል ያሰፈረው፣ በሳምንቱ አጋማሽ ለንባብ የበቃው የልዑል ግርማ ‹‹ምን ልሥራ? እንዴትስ?›› መጽሐፍ ነው፡፡ መጽሐፉ ተግባራዊ የሥራ ፈጠራና የቢዝነስ አመራር ከ55 የኢንተርፕነርሺፕ ቢዝነስ መነሻ ሐሳቦች ጋር መያዙን በመግቢያው አስፍሯል፡፡

የመጽሐፉ ዋጋ 50 ብር ነው፡፡

******************

‹‹የመንገድ በረከት››

‹‹የመንገድ በረከት›› ይለኛል፡፡ የጋዜጠኛ ሔኖክ ሥዩም የጉዞ ማስታወሻ መጽሐፍ፡፡ በቅርቡ የሕትመት ብርሃን ያየው መጽሐፍ ይዘት ጋዜጠኛው በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች ሲንቀሳቀስ የታዘበውን፣ የተመለከተውንና ያጋጠሙትን የጻፈበት የጉዞ ማስታወሻ ነው፡፡

ሀገሬ ሚዲያ ኮሙኒኬሽን ለሪፖርተር በላከው መግለጫ ላይ እንዳስታወቀው፣ ‹‹የመንገድ በረከት›› ዓርብ የካቲት 20 ቀን 2007 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡30 በብሔራዊ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት ድርጅት (ወመዘክር) አዳራሽ ይመረቃል፡፡

የመጽሐፉ ዋጋ 46 ብር ነው፡፡

******************

‹‹ሰኔ 30››

‹‹ሰኔ 30›› የተሰኘው ፊልም የካቲት 15 ቀን በአዲስ አበባና በአዳማ የግል ሲኒማ ቤቶች እንዲሁም የካቲት 23 ቀን በአዶት ሲኒማና ቴአትር ቤት ይመረቃል፡፡ በኃይሉ ዋሴ የተጻፈው ፊልሙ፣ በፍቅረየሱስ ድንበሩ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ሽመልስ አበራ፣ ሰለሞን ሙሄ፣ አዚዛ አህመድ፣ ካሌብ ደሳለኝና ሌሎችም ተውነውበታል፡፡

ፊልሙ የፍቅር ሕይወታቸውን ለመቀጠል ወይም ለመቋጨት ለመወሰን ሰኔ 30 ቀን በተቀጣጠሩ ፍቅረኛሞች መካከል የሚከሰተውን አጋጣሚ የሚያሳይ ሲሆን፣ አንድ ሰዓት ከ42 ደቂቃ ይወስዳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...

አወዛጋቢነቱ የቀጠለው የአዲስ አበባ የጤፍ ገበያ

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤፍ የተከሰተውን የዋጋ ንረት...