በቅሎ፤ አጋሰስ ካህያ ከፈረስ የሚደቀል፣ አባቱ አህያ እናቱ ፈረስ የሚለው፣ የአለቃ ደስታ ተክለወልድ ‹‹ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት›› (1962) ነው፡፡ ባላገሮች ከጥንት ከፍጥረት ስላልነበረ አህያና ፈረስን በማራከብ በሰው ዘዴ ስለተገኘ በምድራችን እንዲህ ያለ በቅሎ አያውቅም ተባለ ይላሉ፤ የስሙም ምክንያት ይህ እንደሆነ ይተርካሉ፡፡ በሌላ በኩል የጭን በቅሎ ሲባል መቀመጫ ሰጋርን ያመለክታል፡፡
በተረታዊ ብሂል ‹‹በቅሎ አባትህ ማነው ቢሉት እናቴ ፈረስ ነች አለ›› ይባላል፡፡