Sunday, June 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየትውልዳችን አዲሱ ፈተና

የትውልዳችን አዲሱ ፈተና

ቀን:

በዳንኤል ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)

የዛሬውን ሐሳብ ለመጻፍ ወረቀትና ቀለም እንዳገናኝ ያደረገኝ በዚህ ሣምንት በጣም የምንወደውና ለኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና የራሱን አሻራ ያሳረፈ ውድ ወዳጃችን ሕይወቱን በማጣቱ ነው፡፡

ይህ ወዳጃችን ከ17 ዓመት በፊት የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የካንሰር ጨረር ሕክምና አገልግሎቱን ሲጀምር በይፋ መርቆ ያስጀመረ ሲሆን፣ በወቅቱ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የጤና አገልግሎት መምሪያ ኃላፊ ነበር፡፡ ዛሬ ከ17 ዓመታት  በኋላ ወዳጃችን በኩላሊት ካንሰር ያውም የዓለም የካንሰር ቀን በሚከበርበት ዕለት ውድ ሕይወቱን አጥቷል፡፡

ታዲያ በወቅቱ የኅብረተሰቡን ካንሰር ላይ ያለውን ግንዛቤ ማስፋት እንደሚያስፈልግ ነበር በንግግሩ የገለፀው አዎን በዚህ ዓመትም የዓለም የካንሰር ቀን ሲከበር ‹‹ከእኛ አያልፍም›› ወይም “not beyond us” በሚል መሪ ቃል ሆኖ የኅብረተሰቡን ግንዛቤ የመጨመርን ዋኛ ዓላማ አንግቧል፡፡

በዓለም ላይ በ2004 ዓ.ም. ብቻ 14 ሚሊዮን አዳዲስ የካንሰር በሽተኞች ሲገኙ ከ8.2 ሚሊዮን በላይ ደግሞ በዚሁ ዓመት ሕይወታቸውን በካንሰር አጥተዋል፡፡ ባሳለፍነው ዓመት በአሜሪካ ከ1.6 ሚሊዮን ሕሙማን ካንሰር ሲገኝባቸው እንደ ዓለም ጤና ድርጅት እንደሚተነብየው በ20 ዓመት ውስጥ በዓመት ከ22 ሚሊዮን በላይ ሰው በካንሰር ሊጠቃ ይችላል፡፡

ካንሰር ምንድን ነው?

ካንሰር ማለት የሰውነታችን ሴሎች ወይም ህዋሳት ከቁጥጥር ውጪ በመውጣት የሚራቡበት መንገድ ሲሆን እነዚህ ሴሎች ከማንኛውም የሰውነታችን ክፍል በመነሳት በደምና ሊምፍ አማካይነት ወደ ሌላ የሰውነት ክፍላችን ሊዛመቱ ይችላሉ፡፡

እነዚህ ሴሎች በብዛት ከመራባታቸውም በላይ የዘወትር ሥራቸውን በመዘንጋት እርስ በርሳቸው በመያያዝ እባጭ (Tumor) በማምጣት በአካባቢው ያሉትን ጤናማ ሴሎችና የሰውነት ክፍሎች ሥራቸውን እንዳይሠሩ ከማወካቸው በላይ አንዳንድ የካንሰር ዓይነቶች ደግሞ አላስፈላጊ ንጥረ ነገር ያመርታሉ፡፡ በእርግጥ ከመቶ በላይ የሚሆኑ የካንሰር ዓይነቶች ሲኖሩ ሁሉም ዓይነት ተመሳሳይ ዓይነት የጉዳት መጠን አይኖራቸውም፡፡

የካንሰር መነሻ ምንድን ነው?

      ብዙውን ጊዜ የካንሰር መነሻ ምን እንደሆነ አይታወቅም፤ ሆኖም በጄኔቲክ (genetic) በቤተሰብ የሚተላለፍ ጤናማ ያልሆነ የአኗኗር ዘይቤ፣ ሲጋራ ማጨስ፣ አልኮል፣ ጤናማ ያልሆኑ ምግቦች መመገብ፣ ከመጠን ያለፈ ውፍረት፣ ኢንፌክሽን በሚያመጡ ጀርሞች፣ በጨረሮችና ጎጂ ኬሚካሎች ምክንያት ለካንሰር ልንጋለጥ እንችላለን፡፡

በወንዶች ላይ የሳንባ፣ የፕሮስቴት፣ የአንጀት፣ የጨጓራና የጉበት ካንሰር፣ በሴቶች ደግሞ የጡት፣ የአንጀት፣ የሳንባ፣ የማህፀን በርና የጨጓራ ካንሰር ከ1-5 በደረጃ ይከሰታሉ፡፡

ካንሰር ብዙውን ጊዜ በዕድሜ የገፉ ሰዎች ላይ የሚከሰት ቢሆንም በሕፃናትና በማንኛውም የዕድሜ ክልል ላይ ያሉ ሰዎችን ሊያጠቃ የሚችል ነው፡፡

ካንሰርን እንዴት መከላከል ይቻላል?

በመጀመሪያ በጤናማ አኗኗርና አመጋገብ ልንከተል ይገባል፤ ማለትም ከሲጋራ፣ ከአልኮልና ሰውነትን አለቅጥ ከሚያወፍሩ ምግቦች መታቀብ ሲኖርብን በየጊዜው ስፖርት ወይም አካላዊ እንቅስቃሴ ማከናወን በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ የዘርፉ ተመራማሪዎች አትክልትና ፍራፍሬ መጠቀም ጠቀሜታ እንዳለው ያስረዳሉ፡፡

በየወቅቱ የሕክምና ምርመራ ማድረግ በተለይም ካንሰር በመጀመሪያ ደረጃ እንዳለ ለማወቅ ስለሚረዳ በቶሎ ሕክምና ከተገኘ በቀላሉ ለመዳን ይቻላል፡፡  እዚህ ላይ እንደ አብነት የጡትና የማህፀን በር ካንሰርን መውሰድ ይቻላል፡፡

የካንሰር ሕክምና

የካንሰር ሕክምና ከመሰጠቱ በፊት የካንሰሩን ዓይነትና ደረጃ በሕክምና መሣሪያዎች በመታገዝ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም የተለያዩ ካንሰሮች የተለያየ ዓይነተኛ ሕክምና ይሰጣቸዋል፡፡ በመድኃኒት፣ በኦፕሬሽን፣ በጨረር ሕክምና እንደ ካንሰሩ ዓይነትና ደረጃ ሊሰጥ ይቻላል፡፡ በተጨማሪም “Immuno therapy” እና “gene therapy” ምርመራ እየተደረገባቸው ይገኛል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የካንሰር ሕክምና በአገራችን ለማስፋፋት በአምስት አዳዲስ ኃይሎች ሕክምናው እየተጀመረ ሲሆን፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርም አዳዲስ የካንሰር መድኃኒቶችን አገር ውስጥ በማስገባት ላይ ይገኛል፡፡ እነዚህ መድኃኒቶች ዋጋቸው እጅግ በጣም ውድ በመሆኑ ሚኒስቴሩ የበጀት ድጎማ እያደረገባቸው ሲሆን ወደፊት በዘላቂነት ዋጋቸው ለተጠቃሚው ተመጣጣኝ የሚሆንበትን ስትራቴጂ ነድፎ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡

በመጨረሻም ሕይወቱን በሙሉ የኅብረተሰብ ጤና እንዲጠበቀ ብሎም በኢትዮጵያ ውስጥ የደም ባንክ አገልግሎት እንዲደራጅ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ የነበረው በቅርቡ በሞት ለተለየን ለዶ/ር ዮሐንስ ከበደ ቤተሰቦችና ጓደኞች መፅናናትን እመኛለሁ፡፡ 

ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊው የብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎት ዳይሬክተር ሲሆኑ፣ በኢሜል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...