በሩሲያ የባህል ማዕከል (ፑሽኪን) አዳራሽ የሩሲያን ብሔራዊ አንድነት ቀን ምክንያት በማድረግ የሙዚቃ ኮንሰርት ተካሂዷል፡፡ በማዕከሉ ጥቅምት 25 ቀን 2010 ዓ.ም. በተካሄደው ኮንሰርት ሩሲያውያኑ ኤሌክሲ ማልኒከቭና ቭላድሚር ዩስቲያንስቴቭ ሥራዎቻቸውን ያቀረቡበት ነበር፡፡ ፒያኖና ሳክስፎን የሚጫወቱት ሙዚቀኞች የሴንት ፒተርስበርግ ሚውዚክ ሐውስ ሙያተኞች ሲሆኑ፣ ዘለግ ላለ ጊዜ ሙዚቃ አስደምጠዋል፡፡ ሁለቱ ሙዚቀኞች ሥራዎቻቸውንና በሩሲያና ሌሎችም አገሮች ከማቅረባቸው ባሻገር የተለያዩ ሽልማቶችም ተበርክቶላቸዋል፡፡ በአዲስ አበባና በሴንት ፒተርስበርግ ከተሞች መካከል ያለው እህትማማችነት በታሰበበት መድረክ ሥራቸውን ሲያቀርቡም አድናቆት ተቸሯቸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ ሩሲያውያንና ኢትዮጵያውያንም ሙዚቃውን ታድመዋል፡፡ የማዕከሉ የዮሴፍ ኃይለማርያም የሥዕል ሥራዎችም በታዳሚዎቹ ተጎብኝተዋል፡፡
-
- ፎቶ በመስፍን ሰሎሞን