Tuesday, November 29, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየመሠረተ ልማት ተቋማት በቅንጅት ለመሥራት ተስማሙ

  የመሠረተ ልማት ተቋማት በቅንጅት ለመሥራት ተስማሙ

  ቀን:

  • ኢትዮ ቴሌኮም በዚህ ዓመት 700 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ዝርጋታ ያካሄዳል

  በፌዴራል መንግሥትና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር የሚገኙ የመሠረተ ልማት ተቋማት፣ ከዚህ በኋላ በአዲስ አበባ የሚያከናውኗቸውን ግዙፍ ፕሮጀክቶች በመናበብ ለመገንባት ረቡዕ ጥቅምት 29 ቀን 2010 ዓ.ም. የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

   በቅርቡ የተቋቋመው የአዲስ አበባ ከተማ የመሠረተ ልማት ቅንጅት፣ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ራሱን አደራጅቶ ኃላፊነቱን እስኪረከብ ድረስ፣ የመሠረተ ልማት ተቋማቱን የማስተባበር ሥራ የፌዴራል የተቀናጀ መሠረተ ልማት ማስተባበርያ ኤጀንሲ እንደሚይዘው፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተናግረዋል፡፡

  በዚህ መሠረት በአዲስ አበባ ከተማ ሰፋፊ ሥራ ያላቸው ኢትዮ ቴሌኮም፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የመንገዶች ባለሥልጣንና የውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣንን ጨምሮ ስድስት የመሠረተ ልማት ተቋማት በቅንጅት እንዲሚሠሩ ታውቋል፡፡

  የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ አንዷለም አድማሴ (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በአዳዲስ የኮንዶሚንየም ቤቶች፣ በአዳዲስ መንደሮችና በኢንዱስትሪ ፓርኮች ተቋማት አካባቢ ትልልቅ ሥራዎች በአዲሱ ስምምነት መሠረት በቅንጅት ይከናወናሉ፡፡

  ኢትዮ ቴሌኮም በተያዘው በጀት ዓመት በተጠቀሱት አዳዲስ አካባቢዎች 700 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸው የድምፅና የምሥል ዳታ ማስተላለፍያ ኮፐርና ፋይበር ኦፕቲክስ ዝርጋታዎች እንደሚያካሂድ ተገልጿል፡፡

  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትም በተለይ ከመሬት በታችና ከመሬት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን የመዘርጋት ዕቅድ አለው፡፡ በተለይ ገላን፣ ኩዬ ፈጬ፣ ቂሊንጦ፣ እንዲሁም ሜክሲኮ አካባቢን የሚያቋርጡ የምሥራቅ ምዕራብ ቀላልና ከባድ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ይገነባሉ ተብሎ ዕቅድ ተይዟል፡፡ በዚህ ፕሮጀክት በአጠቃላይ ስምንት ሺሕ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎች እንደሚተከሉ በወቅቱ ተገልጿል፡፡

  በውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣንም እንዲሁ ከለገዳዲ ማጣሪያ የሚገኘውን 86 ሺሕ  ሜትር ኩብ ውኃ ማስተላለፍ የሚያስችሉ በርካታ መስመሮች፣ የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያን የሚያገናኙ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች በዚህ ዓመት እንደሚገነቡ ተገልጿል፡፡

  በመንገድም ፕሮጀክቶች ደግሞ በርካታ አዳዲስ ፕሮጀክቶች ከመጀመራቸውም በተጨማሪ በመሀል ከተማ በርካታ ኪሎ ሜትሮች የሚሸፍኑ የእግረኛ መንገዶች በታይልስ መሥራት ተፈልጓል፡፡

  እነዚህ ሁሉ ፕሮጀክቶች ከወትሮው በተለየ መንገድ ተቀናጅተው እንደሚካሄዱ ታውቋል፡፡ በመግባቢያ ሰነዱ ላይ እንደተመለከተው ሁሉም የመሠረተ ልማት ተቋማት የሚያካሄዷቸውን ፕሮጀክቶች ዲዛይንና ስፔሲፊኬሽን አዘጋጅተው ሰነዱን ያቀርባሉ፡፡ የሚያቀርቡት ሰነድ የአምስት ዓመቱን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ፣ የከተማውን ማስተር ፕላን፣ እንዲሁም ዓመታዊ ዕቅዳቸውን ታሳቢ ያደረገ ይሆናል ተብሏል፡፡

  በዚህ መሠረት ተቋማቱ በጋራ ተቀናጅተው ይሠራሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ይህ አሠራር ቀደም ብሎ የነበረውን የሀብትና የጊዜ ብክነት ከማስቀረቱም በላይ ለሰዎች አደገኛ የሆነውን ቁፋሮና በትራፊክ ፍሰት ላይ የሚኖረውን ተፅዕኖ እንደሚያስቀር ተገልጿል፡፡

  የፌዴራል የተቀናጀ መሠረተ ልማት ማስተባበሪያ ኤጀንሲ ተጠባባቂ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰሎሞን ገብረ መድኅን እንደገለጹት፣ የመሠረተ ልማት ተቋማት ተቀናጅተው ባለመሥራታቸው በርካታ ችግሮች ተፈጥረዋል፡፡ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት ተቋማቱ ተናበው ለመሥራት መግባቢያ በመፈራረማቸው ትልቅ ለውጥ ይመጣል ሲሉ እምነታቸውን ተናግረዋል፡፡

   

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በችግር የተተበተበው የሲሚንቶ አቅርቦት

  ሲሚንቶን እንደ ግብዓት ተጠቅሞ ቤት ማደስ፣ መገንባት፣ የመቃብር ሐውልት...

  ‹‹የናይል ዓባይ መንፈስ›› በሜልቦርን

  አውስትራሊያ ስሟ ሲነሳ ቀድሞ የሚመጣው በተለይ በቀደመው ዘመን የባህር...

  ‹‹ልብሴን ለእህቴ››

  ለሰው ልጅ መኖር መሠረታዊ ፍላጎት ተብለው ከተዘረዘሩት ውስጥ ልብስ...

  የአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች የምርመራ ውጤት እስከምን?

  በፍቅር አበበ የትምህርት ጥራትን፣ ውጤታማነትንና ሥነ ምግባርን ማረጋገጥ ዓላማ አድርጎ...