Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊግንባታቸው የተጠናቀቁ 33 ሺሕ ኮንዶሚኒየም ቤቶች በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚተላለፉ ታወቀ

ግንባታቸው የተጠናቀቁ 33 ሺሕ ኮንዶሚኒየም ቤቶች በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚተላለፉ ታወቀ

ቀን:

ከ20/80 እና 10/90 በተጨማሪ 40/60ም በዕጣው ተካቷል

በዕጣው አወጣጥ ሥርዓት ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይገኛሉ ተብሏል

ካለፈው ዓመት ሚያዝያ ወር 2006 ዓ.ም. ጀምሮ በተለያዩ ጊዜያት በዕጣ ለባለዕድለኞች ይተላለፋሉ ሲባሉ የነበሩት የኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ፣ በሚቀጥለው ሳምንት እሑድ የካቲት 29 ቀን 2007 ዓ.ም. እንደሚወጣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡

መሠረተ ልማቶች ባለመሟላታቸውና የቤቶቹ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ባለመጠናቀቁና በሌሎችም ምክንያቶች፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ መተላለፍ ሳይችሉ ቆይተው ወደ 2007 ዓ.ም. መሸጋገራቸው ይታወሳል፡፡ ከሁለት ወራት በፊት 73 ሺሕ ቤቶች እንደሚተላለፉ የተገለጸ ቢሆንም፣ የዕጣ አወጣጡ በሚቀጥለው ሳምንት ከተጀመረ በኋላ በሁለት ተጨማሪ ዙሮች እንደሚጠናቀቅ ምንጮች ተናግረዋል፡፡

የመጀመርያውና በአብዛኛው 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የያዘው ዕጣ የካቲት 29 ቀን 2007 ዓ.ም. ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በተገኙበት 33 ሺሕ ቤቶች በዕጣ እንደሚተላለፉና 10/90 እና 40/60ንም ያካተተ እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡ ቀሪዎቹ ቤቶች እስከ ሰኔ 30 ቀን 2007 ዓ.ም. ድረስ በሁለት ዙር እንደሚተላለፉ፣ ሁሉም ቤቶች ግንባታቸው መቶ በመቶ የተጠናቀቀ በመሆኑ ለባለዕድለኞች ቁልፍ ወዲያው (ቢበዛ በሳምንት ውስጥ)  እንደሚሰጥ ምንጮች አክለዋል፡፡

የዘንድሮው የጋራ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ከሌላው ጊዜ ለየት ባለ ሥርዓት እንደሚከናወን የገለጹት የሪፖርተር ምንጮች፣ በዕጣ አወጣጡ ሥነ ሥርዓት ላይ ለሚገኙ ባለሥልጣናትና ታዳሚዎች ግብዣ ለማድረግ፣ ሆቴሎች ለዝግጅቱ እንዲወዳደሩ ጨረታ የወጣ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ቁጥራቸው 17 የሚሆኑ ሆቴሎች በጨረታው መሳተፋቸውን የገለጹት ምንጮች፣ ጨረታው የካቲት 19 ቀን 2007 ዓ.ም. እንደሚከፈትም ተናግረዋል፡፡ አሸናፊው ሆቴል ሙሉ የምሳ ግብዣ ከማድረጉም በተጨማሪ፣ ዕጣው በሚወጣበት ቦታ እሽግ ውኃዎችን እንደሚያቀርብ ተጠቁሟል፡፡ ለዝግጅቱ የታቀደው ወጪ ምን ያህል እንደሆነ ምንጮች ማወቅ አለመቻላቸውንም አክለዋል፡፡

ዕጣ የሚወጣባቸውና ግንባታቸው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀው የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚገኙት አራት ኪሎ ባሻ ወልዴ ችሎት፣ የካ አባዶ፣ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቱሉ ዲምቱ (ከአሥር ሺሕ በላይ ቤቶች) ቦሌ ቡልቡላ (አብዛኛው በልማት ለሚነሱ የተመደበ ነው) እና በልደታ መልሶ ማልማት መሆናቸው ታውቋል፡፡

           

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...