‹‹የትግሉ ፋና ወጊ በሆነው ደደቢት በረሃ የተገኘሁት ለሽርሽር ሳይሆን፣ በሺሕ የሚቆጠሩ ታጋዮች ሕይወት የከፈሉበትን ዓላማ በማሳካት የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ቃል ለመግባት ነው፡፡››
የሕወሓት 40ኛ ዓመት ክብረ በዓል ሲከበር፣ የትጥቅ ትግል በተጀመረበት የደደቢት በረሃ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሕወሓት ታጋዮች ሕይወታቸውን የከፈሉበትን ዓላማ ለማሳካትና አደራቸውን ወደላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር፣ ኪራይ ሰብሳቢነትና ሙስና ከምንጫቸው መድረቅ አለባቸው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም መልካም አስተዳደር ማስፈንና ፀረ ዴሞክራሲ ተግባራትን መታገል እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡ ለዚህም ወቅቱ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት መክፈል የግድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በምሥሉ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ‹‹ክሹፍ›› በመባል የሚታወቀውንና በትግሉ ጊዜ የሚዘወተረውን የሕወሓት ታጋዮች መለያ አንገታቸው ላይ ጠምጥመው ይታያሉ፡፡