Wednesday, February 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየእንግሊዝ መንግሥት ለኢትዮጵያ የሚሰጠው ዕርዳታ ከምግብ ዋስትና ውጪ ባሉ መስኮች ላይ ይውላል...

የእንግሊዝ መንግሥት ለኢትዮጵያ የሚሰጠው ዕርዳታ ከምግብ ዋስትና ውጪ ባሉ መስኮች ላይ ይውላል አለ

ቀን:

የእንግሊዝ መንግሥት ለኢትዮጵያ በየዓመቱ የሚሰጠውን የሰብዓዊና የምግብ ዋስትና ዕርዳታ ወደ ሌሎች መስኮች እንደሚያዞር አስታወቀ፡፡ በየዓመቱ ይሰጥ የነበረው ዕርዳታ ባስቀመጠው የድርጊት መርሐ ግብር መሠረት እንደሚቀጥል ይፋ አድርጓል፡፡

የእንግሊዝ መንግሥት በድረ ገጹ ይፋ እንዳደረገው፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እየታየ ባለው የምዕተ ዓመቱ የልማት ግቦች አፈጻጸም ስኬት ምክንያት የአገሪቱ ፍላጎት እየተለወጠ መጥቷል፡፡ በዚህም ሳቢያ እንግሊዝ የሥራ ዕድል በሚፈጥሩ፣ ገቢ በሚያስገኙና አገሪቱ ራሷን እንድትችል በመርዳት ድህነትን በሚያስቀሩ መስኮች ላይ የሚያተኩር ድጋፍ እንደምታደርግ አስታውቋል፡፡

ለጤና፣ ለትምህርትና ለውኃ ፕሮግራሞች የሚሰጠው ተጨማሪ ፈንድ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ለኢኮኖሚያዊ ተግባራት ይውላል የተባለው የዕርዳታ ገንዘብ እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡ በትምህርት፣ በጤናና በውኃ አቅርቦት መስክ የታዩትን ለውጦች በመመርኮዝ ከእንግዲህ በኋላ ለመሠረታዊ አገልግሎቶች ሲሰጥ የቆየው ዕርዳታ እንደማይኖር ታውቋል፡፡ ሆኖም እ.ኤ.አ. እስከ 2016 ለኢትዮጵያ ይሰጣል የተባለው ድጋፍ እንደማይቋረጥ የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ የልማት ተቋም (DFID) ይፋ አድርጓል፡፡

የልማት ተቋሙ ከጥቂት ወራት በፊት አሻሽሎ ይፋ ያደረገው ሪፖርት እንደሚጠቁመው፣ እ.ኤ.አ. ከ2012 ጀምሮ ባሉት አምስት ዓመታት ውስጥ በየዓመቱ በአማካይ ከ265 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ዕርዳታ ለኢትዮጵያ ይሰጣል፡፡ ትምህርት፣ ጤና፣ ውኃና ሳኒቴሽን፣ ሰብዓዊ ዕርዳታ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ዋና ዋና ዕርዳታው የሚያተኩርባቸው ዘርፎች ናቸው፡፡

በመሆኑም በዚህ ዓመት በዓይነትና በገንዘብ ለኢትዮጵያ የሚሰጠው የዕርዳታ መጠን ከዓመት ዓመት እየጨመረ መምጣቱን የሚጠቁም ነው፡፡ በዚህ ዓመት መጨረሻ የሚለቀቀውን 289.7 ሚሊዮን ፓውንድ ጨምሮ፣ በመጪው ዓመት 303 ሚሊዮን ፓውንድ ለኢትዮጵያ ሊለቀቅ እንደሚችል የልማት ተቋሙ መረጃ ያሳያል፡፡

የእንግሊዝ ዜግነት ያላቸው የግንቦት ሰባት ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የመን ሰነዓ አውሮፕላን ማረፊያ በሰኔ 2006 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ውለው ለኢትዮጵያ በመተላለፋቸው ምክንያት፣ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የተወሰኑ የእንግሊዝ ፓርላማ አባላት በኢትዮጵያ ላይ እንግሊዝ ጫና እንድታደርግና ዕርዳታ እንድታቋርጥ መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነው አሁን እንግሊዝ ዕርዳታውን አጠናክራ እንደምትቀጥል እየገለጸች ያለችው፡፡

በሌላ በኩል የአውሮፓ ኅብረት እ.ኤ.አ. ከ2010 ጀምሮ የሚታሰብ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ መጠን ያለው ኦፊሴላዊ ዕርዳታ ለኢትዮጵያ የሚለቀቅበትን ስትራቴጂ፣ እዚህ አገር በሚንቀሳቀሱ የኅብረቱ 22 አባል አገሮች አማካይነት በቅርቡ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

 

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ጥቁር የመልበስ ውዝግብና የእምነት ነፃነት በኢትዮጵያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ኅዳር ወር ላይ በፓርላማ...

የኢንሹራንስ ዘርፉን የሚቆጠጠር ገለልተኛ ተቋም ለመመሥረት እንቅስቃሴ ተጀመረ

ከ70 በላይ አዳዲስ የፋይናንስ ተቋማት ዘርፉን ሊቀላቀሉ ነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ...

እስቲ አንገፋፋ!

እነሆ መንገድ። ጊዜና ሥፍራ ተጋግዘው በውስንነት ይዘውናል። መፍጠን ያቃተው...