Thursday, February 29, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየአጥፍቶ መጥፋት ወንጀል ሊፈጽሙ ነበር የተባሉ ተጠርጣሪ የአልሸባብ አባላት ተከሰሱ

የአጥፍቶ መጥፋት ወንጀል ሊፈጽሙ ነበር የተባሉ ተጠርጣሪ የአልሸባብ አባላት ተከሰሱ

ቀን:

ሕዝብ የሚበዛባቸው ኤድና ሞልና ፍሬንድሺፕ ዒላማ ነበሩ ተብሏል

ዜግነታቸው ሶማሊያዊ የሆኑና በተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀው አልሸባብ አባል ናቸው የተባሉ አምስት ተጠርጣሪ ሶማሊያውያን፣ በአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ በሚበዛባቸው የመዝናኛ ሥፍራዎች የአጥፍቶ መጥፋት ወንጀል ለመፈጸም በመዘጋጀት ላይ እያሉ በቁጥጥር ሥር ውለው ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

የአጥፍቶ መጥፋት ወንጀል በመፈጸም በመንግሥት ላይ ተፅዕኖ አሳድረው፣ ኢትዮጵያ እያደረገች ያለውን የፀረ ሽብርተኝነት ትግል ለማዳከምና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለማፈራረስ ከአልሸባብ ተልዕኮ በመቀበል፣ በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ በዕቅድ ላይ እንዳሉ በክትትል መያዛቸውን የተመሠረተባቸው የክስ ዝርዝር ያስረዳል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ተጠርጣሪዎቹ መቀመጫቸውን በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልል አዳማ ከተማ ውስጥ አድርገው ይንቀሳቀሱ እንደነበር በክሱ ተጠቅሷል፡፡ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ክስ የመሠረተባቸው ተጠርጠሪዎች ሁሴን አብዲኑር ኢብራሂም፣ ሙስጠፋ አብዱላሂ ኩልምዬ፣ ሙስጠፋ አህመድ መሐመድ፣ አብዲ ዓሊ ኑርና ፈርሃን መሐመድ መዓሊን ይባላሉ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ሕዝብ በሚበዛባቸው የመዝናኛ ሥፍራዎች ላይ የአጥፍቶ መጥፋት ወንጀል ለመፈጸም በዝግጅት ላይ እንደነበሩ የሚያስረዳው ክሱ ኤድና ሞል ማቲ ሲኒማና ፍሬንድሺፕ ሕንፃዎች ዒላማ ከተደረጉት ሥፍራዎች ውስጥ እንደሚገኙበት ይጠቁማል፡፡

ሁሴን አብዲኑር ኢብራሂም የተባለው ተጠርጣሪ ትክክለኛ ቀኑ ባልታወቀበት በሐምሌ ወር 2004 ዓ.ም. በሞቃዲሾ ከተማ የአባቱ ስም ባልታወቀው ዳዲር በተባለ የአልሸባብ አመራር አማካይነት አባል መሆኑ በክሱ ተጠቅሷል፡፡ ለሽብር ድርጊቱ ማስፈጸሚያ ገንዘብ በመቀበል ኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጸሙ የሽብር ድርጊቶችን የማስተባበር የማቀነባበርና የማስፈጸም ኃላፊነት መቀበሉም ተጠቁሟል፡፡ መልዕክት መለዋወጥ እንዲችል የተንቀሳቃሽ ስልክ (ቁጥሩ ተጠቅሷል) ሞቃዲሾ ለሚገኘው የአልሸባብ አመራር ዳዲር በመስጠት፣ አዲስ አበባ ተመልሶ የሚሰጠውን ተልዕኮ ሲጠባበቅ እንደነበር ተገልጿል፡፡

የአልሸባብ አመራር ነው የተባለው ዳዲር በሐምሌ ወር 2006 ዓ.ም ወደ ሁሴን ደውሎ፣ ‹‹በስልክ የማይነገር ተልዕኮ ስለሚሰጥህ ወደ ሞቃዲሾ መምጣት አለብህ፤›› በማለት፣ የትራንስፖርት 200 ዶላር ተልኮለት ወደ ሞቃዲሾ በመሄድ ከአመራሩ ጋር መገናኘቱ ተብራርቷል፡፡

አልሸባብ በኢትዮጵያ ውስጥ የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ዕቅድ ማውጣቱን፣ ሁለት አጥፍቶ ጠፊዎችን መመደቡንና መታወቂያ እንዲያዘጋጅላቸው ወደ ኢትዮጵያ የሚያስገባቸው ሰው እንዲፈልግ፣ ለየብቻቸው በጥሩ ሁኔታ በማስቀመጥ አዲስ አበባን እያዘዋወረ እንዲያለማምዳቸውና ጥቃቱን ለመፈጸም ሕዝብ የሚበዛባቸውን ቦታዎች በማጥናት እንዲያሳያቸው፣ በሞያሌ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡትን ፈንጂዎች ለአጥፍቶ ጠፊዎቹ እንዲሰጣቸው፣ ከዳዲርና ከሌሎች አልሸባብ አመራሮች ጋር የኢሜል አድራሻ በመጠቀም እንዲገናኝ ከነይለፍ ቃሉ መቀበሉንና ሌሎች ዝርዝር ትዕዛዞችን መቀበሉን ክሱ ያስረዳል፡፡

ሁሴን አብዲኑር የተባለው ተጠርጣሪ ወደ አዲስ አበባ ከተመለሰ በኋላ አብዲ ዓሊ ኑር በተባለው አራተኛ ተጠርጣሪ የተዘጋጀውን ሐሰተኛ የኢትዮጵያ ሶማሌ የነዋሪነት መታወቂያ ኑሪ በተባለች ግለሰብ አማካይነት ቀኑ ባልታወቀበት ነሐሴ ወር 2006 ዓ.ም. በማውጣት፣ ወደ ሶማሊያ ሐርጌሳ ልኮለት ሙስጠፋ አብዱላሂ ለተባለው ሁለተኛ ተከሳሽ እንደደረሰው ክሱ ያብራራል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ጥናት በማድረግ ሕዝብ የሚበዛባቸው ቦታዎች ኤድና ሞል ማቲ ሲኒማ፣ ፍሬንድሺፕ፣ ቦሌና ሳሪስ መሆናቸውን የአልሸባብ አመራር ነው ለተባለው ዳዲር፣ አንደኛ ተጠርጣሪ ሁሴን አብዲኑር በስልክ መንገሩንም ክሱ አካቷል፡፡ አጥፍቶ የመፋጥቱን ተግባር የሚፈጽሙት ሁለተኛ ተከሳሽ ሙስጠፋ አብዱላሂና አብድልፈታህ መሐመድ የተባሉት ተጠርጣሪዎች ላይ የሚጠመደው ፈንጂ፣ በሪሞት ኮንትሮል የሚፈነዳ መሆኑን ዳዲር እንዲያውቅ መደረጉንና በቂ ዝግጅት አድርጎ ሲጠባበቅ እንደነበር ክሱ ያስረዳል፡፡

በአጠቃላይ ሁሴን አብዲኑር የተባለው አንደኛ ተከሳሽና ተጠርጣሪ ከአልሸባብ አመራሮች ጋር በአካል በስልክና በተለያዩ የኢንተርኔት መገናኛ ዘዴዎች አማካይነት ግንኙት በማድረግ የአጥፍቶ መጥፋት ድርጊትን በበላይነት በማስተባበር በሰዓት የተሞላ ፈንጂ ታጥቆ፣ በሕዝብ ወስጥ ተቀላቅሎ በማፈንዳት በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ለማድረስ ሲጠባበቁ የነበሩ በመሆናቸው፣ በፈጸሙት የሽብር ድርጊቶችን ለመፈጸም ማቀድ ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸዋል፡፡

በተጠርጣሪዎቹ ላይ በአጠቃላይ ሦስት ክሶች የተመሠረቱባቸው ሲሆን፣ ክሶቹም ሐሰተኛ የምስክር ወረቆቶችን የመገልገል ወንጀል፣ ሐሰተኛ ሰነዶችን የማዘጋጀትና የሽብርተኝነት ወንጀል ለመፈጸም ማቀድ ወንጀል ናቸው፡፡

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...