Monday, October 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበሐሰተኛ ማዕረግ የማጭበርበር ወንጀል የተፈረደባቸው ሳሙኤል ዘሚካኤል አዲስ ክስ ተመሠረተባቸው

በሐሰተኛ ማዕረግ የማጭበርበር ወንጀል የተፈረደባቸው ሳሙኤል ዘሚካኤል አዲስ ክስ ተመሠረተባቸው

ቀን:

‹‹ዶ/ር ኢንጂነር ነኝ›› በሚል ሐሰተኛ ማዕረግ በማጭበርበር ወንጀል ተርጥረው፣ ከተመሠረቱባቸው ሦስት ክሶች አንዱን ክደው በሁለቱ ጥፋተኛ የተባሉት አቶ ሳሙኤል ዘሚካኤል አዲስ ክስ ተመሠረተባቸው፡፡

ሰሞኑን በዮድ አቢሲኒያ ባለቤት አቶ ትዕዛዙ ኮሬ አዲስ ክስ የተመሠረተባቸው አቶ ሳሙኤል፣ ‹‹30,000 ብር ተበድረው ክደውኛል›› ተብለው ነው፡፡

በወቅቱ ‹‹ዶ/ር ኢንጂነር›› ተብለው ይጠሩ የነበሩት አቶ ሳሙኤል፣ ወደ አቶ ትዕዛዙ በመሄድ፣ ‹‹ሰው ገጭቼ ሊሞትብኝ ነውና 30,000 ብር አበድረኝ፤›› ብለዋቸው 30,000 ብር የሰጧቸው ቢሆንም፣ በተደጋጋሚ ሲጠይቋቸው ሊከፍሏቸው አለመቻላቸውን ባቀረቡት ክስ አስረድተዋል፡፡

አቶ ትዕዛዙ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 692 ማለትም፣ ‹‹ማንም ሰው የማይገባ ብልፅግና ለራሱ ለማግኘት፣ ወይም ለራሱ ለማስገኘት በማሰብ አሳሳች የሆኑ ነገሮችን በመናገር፣ የራሱን ሁኔታ በመሰወር ወይም መግለጽ የሚገባውን ነገር በመደበቅ፣ የሌላውን ሰው የተሳሳተ እምነት ወይም ግምት በመጠቀም፣ ሌላውን ሰው አታሎ የራሱን ወይም የሦስተኛ ወገንን ጥቅም የሚጎዳ አድራጎት እንዲፈጽም ያደረገ እንደሆነ…›› የሚለውን የሕግ ድንጋጌ በመጥቀስ ክስ መሥርተዋል፡፡

ክሱ የቀረበለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ክሱን ለመስማት ለመጋቢት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

አቶ ሳሙኤል ቀደም ብሎ በአምባሳደር ልብስ ስፌት ፋብሪካ ባለቤት አቶ ሰዒድ መሐመድ ከተመሠረተባቸው ሦስት ክሶች አንዱን መካዳቸውንና ሁለቱን ማመናቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በካዱት ክስ ላይ ዓቃቤ ሕግ ምስክሮች አሰምቶ ለመጋቢት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. ለብይን ተቀጥረዋል፡፡ ባመኑባቸው ሁለት ክሶች ጥፋተኛ ተብለው የእስራት ቅጣት እንደተጣለባቸው መዘገባችን ይታወሳል፡፡

አቶ ሳሙኤል የሐሰት ማዕረግ እየተጠቀሙ የተለያዩ የማጭበርበር ተግባር ፈጽመዋል የሚል መረጃ በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን በመነገሩ ምክንያት ወደ ኬንያ ሸሽተው የነበሩ ቢሆንም፣ የፌዴራል ፖሊስ በኢንተርፖል አማካይነት እንዳመጣቸው አይዘነጋም፡፡ እሳቸው ናይሮቢ በነበሩበት ወቅት፣ አሁን ክስ የመሠረቱትን አቶ ትዕዛዙን ጨምሮ የተለያዩ ግለሰቦች በአቶ ሳሙኤል እንደተጭበረበሩ የገለጹ ቢሆንም፣ ከአምባሳደር ልብስ ስፌት ፋብሪካ ባለቤት አቶ ሰዒድ በስተቀር ማንም ወደ ፍርድ ቤት ሄዶ ክስ የመሠረተ አልነበረም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተመድንና ዓለም አቀፋዊ ሕግን ከእነ አሜሪካ አድራጊ ፈጣሪነት እናድን!

በገነት ዓለሙ በእኔ የተማሪነት፣ የመጀመርያ ደረጃ ተማሪነት ጊዜ፣ የመዝሙር ትምህርት...

የሰላም ዕጦትና የኢኮኖሚው መንገራገጭ አንድምታ

በንጉሥ ወዳጅነው ፍራንክ ቲስትልዌይት የተባሉ አሜሪካዊ ጸሐፊ ‹‹The Great Experiment...

ድህነት የሀብት ዕጦት ሳይሆን ያለውን በአግባቡ ለመጠቀም አለመቻል ነው

በአንድነት ኃይሉ ድህነት ላይ አልተግባባንም፡፡ ብንግባባ ኖሮ ትናንትም ምክንያት ዛሬም...