Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኢትዮጵያ ከግብፅና ከሱዳን ጋር በካርቱም እየመከረች ነው

ኢትዮጵያ ከግብፅና ከሱዳን ጋር በካርቱም እየመከረች ነው

ቀን:

ጥናት የሚያደርጉ ድርጅቶችን ይመርጣሉ

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ ሁለት የተፅዕኖ ሥጋቶችን ለማጥናት በተስማሙት መሠረት የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን ሚኒስትሮችና ባለሙያዎች ጥናቱን ለማካሄድ የቀረቡ ድርጅቶችን ለመምረጥ ካርቱም ላይ ተገናኝተው እየመከሩ ነው፡፡

በሱዳን ካርቱም እየተካሄደ የሚገኘውን ስብሰባ የሦስቱ አገሮች የውኃ ሚኒስትሮችና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በጋራ ከፍተውታል፡፡ በሚኒስትሮቹ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት አቅጣጫ ከተሰጠ በኋላ በሦስቱ አገሮች የተቋቋመው የጋራ ኮሚቴ ከሐሙስ ጀምሮ ዝግ ስብሰባ በማድረግ፣ የቴክኒክና የፋይናንስ ፕሮፖዛላቸውን ካቀረቡ አራት ኩባንያዎች መካከል አንድ ወይም ሁለት ኩባንያዎችን እንደሚመርጡ ይጠበቃል፡፡

ኩባንያዎቹ ለሦስቱም አገሮች ፕሮፖዛላቸውን ያቀረቡ ሲሆን፣ አገሮቹ በባለሙያዎቻቸው አማካይነት የተናጠል ግምገማ ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ ውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር የወሰንና ወሰን ተሻጋሪ ወንዞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተሾመ አጥናፉ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

ከአራቱ ኩባንያዎች መካከል ሁለቱ የፈረንሣይ ኩባንያዎች ቢአርኤል ኢንጂነርስና አርቴል ዴልታረዝ የሚባሉ ናቸው፡፡ ከተቀሩት ኩባንያዎች መካከል ስሜክ የተባለው የኔዘርላንድ ኩባንያና አንድ የአውስትራሊያ ኩባንያ ናቸው፡፡

ቢአርኤል ኢንጂነርስ በኃይድሮ ኢንጂነሪንግ የማማከርና የዲዛይን ፕሮጀክቶችን በመሥራት በዓለም ደረጃ የታወቀ ነው፡፡ ይህ ኩባንያ ዋና መቀመጫው በፈረንሣይ  ሲሆን፣ በ80 አገሮች የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ከዓለም ባንክ፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክ፣ ከስዊድንና ከጀርመን ልማት ባንኮች ጋር በመሆን እንዳከናወነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ የአፍሪካ አገሮች የሚንቀሳቀስና ከአጠቃላይ ገቢውም 20 በመቶ የሚሆነውን የሚያገኘው በአፍሪካ ከሚገኙ ፕሮጀክቶች መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሦስቱ አገሮች ያቋቋሙት የጋራ ኮሚቴ እስከ መጪው እሑድ ድረስ በመምከር ሊጠኑ የተፈለጉትን ሁለት ጥናቶች በጋራ ማጥናት የሚችል አንድ ኩባንያ ወይም በተናጠል ለማጥናት ሁለት ኩባንያዎችን ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህ ከሆነ በቀጣዮቹ ሳምንታት የኮንትራት ፊርማ በአዲስ አበባ ይከናወናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ሦስቱ አገሮቹ በጋራ እንዲያጠኗቸው በዓለም አቀፍ ባለሙያዎች የተሰጠው ምክረ ሐሳብ ሁለት ሲሆን፣ አንደኛው የህዳሴው ግድብ በተለያዩ የዝናብ ወቅቶች የሚሞላበትና የሚለቀቅበት ሞዴል (ኃይድሮ ሲሙሌሽን ሞዴል) ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ግድቡ በታችኛው የተፋሰሱ አገሮች ላይ ማለትም በግብፅና በሱዳን ላይ ሊያስከትል የሚችለው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖን የሚመለከት ነው፡፡

  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...