Friday, December 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለኢንዱስትሪዎች የሚለቀቀው የኤሌክትሪክ ኃይል ራሱን በቻለ መስመር እንዲስተናገድ ተወሰነ

ለኢንዱስትሪዎች የሚለቀቀው የኤሌክትሪክ ኃይል ራሱን በቻለ መስመር እንዲስተናገድ ተወሰነ

ቀን:

ኢንዱስትሪ ዞኖችና ከተሞች የሚጠቀሙበት የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር እንዲለያይና ራሱን በቻለ መስመር እንዲስተናገድ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ጽሕፈት ቤቱ ከዚህ ውሳኔ በተጨማሪ፣ የኤሌክትሪክ ቆጣሪና ትራንስፎርመር ለማስገባት ክፍያ ፈጽመው እየተጠባበቁ የሚገኙ አካላት፣ በወቅቱ የገበያ ዋጋ እየተሰላ ተጨማሪ ክፍያ እንዲፈጽሙ መጠየቃቸው አግባብ አይደለም ብሏል፡፡

በአገሪቱ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የተለየና ራሱን የቻለ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ስለሌላቸው፣ የሚገኙበት ከተማ ከሚጠቀመው መስመር ኃይል እየወሰዱ ሥራቸውን ሲያካሂዱ ቆይተዋል፡፡

ኢንዱስትሪዎች በባህሪያቸው የሚፈልጉት የኤሌክትሪክ ኃይል ከፍተኛ በመሆኑ፣ በኤሌክትሪክ መስመሩ የሚቀርበው ኃይል በቂ ሆኖ አልተገኘም ተብሏል፡፡ ሰሞኑን ከአማራ ክልል ነዋሪዎች ጋር የተወያዩት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ ኢንዱስትሪ ዞኖች ራሱን የቻለ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር እንዲኖራቸው መወሰኑን አስታውቀዋል፡፡

አዲስ አበባና ድሬዳዋን ጨምሮ ዘጠኙም ክልሎች ለኢንዱስትሪ የሚሆኑ ቦታዎችን በማዘጋጀት ለአልሚዎች ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡ ከቅርብ ዓመታት ወዲህም በተለይ ትላልቆቹ ከተሞች የኢንዱስትሪ ዞኖችን እያቋቋሙ ይገኛሉ፡፡ የፌዴራል መንግሥት በተመረጡ አምስት ከተሞች የኢንዱስትሪ ዞኖችን በማቋቋም ላይ ይገኛል፡፡

እነዚህ የኢንዱስትሪ ዞኖች ራሱን የቻለ የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር እንደሚኖራቸው ተገልጿል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በነባሮቹ የኢንዱስትሪ ዞኖች ከከተሞች ጋር የኤሌክትሪክ ኃይል እንዳይጋሩ ለማድረግ ራሱን የቻለ የኃይል መስመር ይገባላቸዋል ተብሏል፡፡

ይህ የሚሆንበት ምክንያት የኃይል መቆራረጥ እንዳይኖር ለማድረግ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉትም በአሁኑ ጊዜ የኃይል እጥረት የለም፡፡ ነገር ግን ያሉት ሰብስቴንሽኖች አስፈላጊውን ኃይል የመያዝ አቅም የሌላቸው በመሆኑ፣ አቅማቸውን የሚያሳድጉ ሥራዎች እየተሠሩ ነው፡፡ የሰብስቴሽኖችን አቅም ለማሳደግ የሚያስችሉ ዕቃዎች ከውጭ እየገቡ ነው፡፡

በርካታ ባለሀብቶችና ግለሰቦች ትራንስፎርመርና ቆጣሪ እንዲገባላቸው ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ክፍያ ፈጽመው እየተጠባበቁ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ክፍያ በተፈጸመበት ዓመት እነዚህ ዕቃዎች ሳይተከሉ ከሦስትና ከአራት ዓመት ቆይታ በኋላ አሁን ባለው የገበያ ዋጋ የተሰላ ሒሳብ መጠየቁ ቅሬታ አስነስቶ ነበር፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ጉዳይ ላይ አዲስ ትዕዛዝ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ተሰጥቷል ብለዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት፣ ችግሩ የተጠቃሚዎች ባለመሆኑ መክሰር ካለበት መንግሥት ይከስራል እንጂ፣ ተጠቃሚዎች ተጨማሪ ክፍያ ሊጠየቁ አይገባም፡፡ ድርጅቱ ተጨማሪ ክፍያ እንዳይጠይቅ ትዕዛዝ መሰጠቱንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...