አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- 3 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) የተከተፈ ናይል ፐርች
- 1 ዝንጣፊ ሠላጣ
- 3 የሾርባ ማንኪያ ማዮኔዝ ሶስ
- 2 ራስ የተገረደፈ ቀይ ሽንኩርት
- 2 ፍሬ ሎሚ
- 1 የሻይ ማንኪያ ጨው
- 1 የሻይ ማንኪያ ነጭ ቁንዶ በርበሬ
አዘገጃጀት
- ዓሣውን በደንብ አጥቦ፣ አንድ የተከተፈ ሎሚ ባለበት ውኃ መቀቀል፤
- ሲበስል አውጥቶ ውኃውን ማጠንፈፍ፤
- አጥንት ካለው በጥንቃቄ ለቅሞ በትንንሹ መክተፍ፤
- ለጋውን ሰላጣ መርጦ በደንብ ካጠቡ በኋላ በቀጫጭኑ መክተፍና ከሽንኩርቱ፣ ከተከተፈው ዓሣ፣ ከማዮኔዘ ሶስ፣ ጨውና ነጭ ቁንዶ በርበሬ ጋር በመቀላቀል መለወስ፤
- ቀሪውን ሎሚ ለሁለት ከፍሎ ለገበታ ማቅረብ፡፡
[ሎሚው አብሮ የሚቀርበው ከላዩ ጨምቆ በመጨመር ለመመገብ ወይም ከበሉ በኋላ ለመምጠጥ ነው፡፡]
- ደብረወርቅ አባተ፣ የውጭ ምግቦች አዘገጃጀት፣ 1993 ዓ.ም.